በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ሐምሌ 10/2013 እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያስታወቀው ከ23 ዓመት በታች የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ተካፋይ የሆኑ ሀገራት የወዳጅነት ጨዋታ እያደረጉ ይገኛል።የዘንድሮ የሴካፋ አዘጋጅ አገር የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ቡድን እንደ ተለመደው ከመድን ቡድን ጋር ዛሬም የወዳጅነት ጨዋታ አድርጎ 2 ለ 1 አሸንፏል። እንደሚታወሰው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት ብሔራዊ በድኑ ከሳምንታት በፊት ከመድን ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ማድረጉ አይዘነጋም።
በተያያዘ ዜና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከ23 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ሁለት ተጨዋቾችን አሰናብተው ሌላ ሁለት ለማካተት ጥሪ አቅርበዋል። አሰልጣኙ ያሰናበቷቸው ተጨዋቾት በቅርቡ ለብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች የኮቪድ ክትባት መሠጠቱ ይታወሳል። ነገር ግን ሁለቱ ተጨዋቾች በክትባቱ ላይ ባላቸው የግል አመለካከት “አንከተብም” በማለታቸው ግብጠባቂው ምንተስኖት አሎ እና ዘንድሮ ድንቅ አቋም ላይ የሚገኘው አጥቂው ይገዙ ቦጋለ ከቡድኑ ተቀንሰዋል። የኢትዮጵያ ዋናው ብሔራዊ ቡድን በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ የሚሰተፍ ይሆናል። በቀጣይ ለብሔራዊ ቡድኑ የሚሰጠው የኮቪድ ክትባት አንከተብም ለሚሉት ተጨዋቾች መፍትሄው ማሰናበት ?
ምርመራውን ካለፉ በቂ ነው አለፍላጎታቸው ተከተቡ ማለት አይነ ስውር ነህና እኔ ልምራህ ከማለት አይተናነስም፡፡