የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በአዲሱ ኮንቬንሽን መሰረት በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የግብ ጠባቂዎች የአሰልጣኝነት ስልጠና እና የአካል ብቃት ስልጠና እንዲሚጀመር በወሰነው መሰረት በአልጄሪያ የመጀመሪያውን ስልጣና ላለፉት ሶስት ሳምንታት በተሳካ መልኩ አካሄዶ ዛሬ ፍፃሜ አግኝቷል።
በMay 7 ተጀምሮ ላለፉት ሶስት ሳምንታት ሲካሄድ የነበረውን የመጀሪያው የግብ ጠባቂዎች ስልጠናን 28 የአልጄሪያ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኞች የተከታሉ ሲሆን ስልጠናውን በካፍ የልማት ዳይሬክተር ራውል ቺፔንዳ እና በፊፋ ሄሬዲያ አሌሃንድሮ አልፍሬዶ እንዲሁም በካፍ ፊፋ ብቸኛው ተወካይ ኢሌት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ሰጥተዋል።
የአልጄሪያ ቴክኒካል ዳይሬክተር ሙስጠፋ ቢስክሪ ስልጠናውን አስመልክቶ እንደተናገሩት ስልጠናው መጀመሩ በመላ አፍሪካ ያለውን የግብ ጠባቂዎችን ደረጃ የሚያሻሽል በመሆኑ እጅግ ጠቃሚ ነው ብለዋል። ስልጠናው በቀጣይ በሁሉም የአፍሪካ አገራት እንደሚቀጥል ካፍ በድህረገፁ ዘግቧል።
ዛሬ ፍፄሜ ላገኘውና በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ስልጠና ለሰጡት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱን እና ለሁለቱም ባለሙያዎች የአልጄሪያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምስጋና ስጦታ አበርክቷል።
በተያያዘ መረጃ ዛሬ ምሽት ከ 17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ከሌሊቱ 6:00 በሴኔጋልና በሞሮኮ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የሚካሄድ ሲሆን ጨዋታ ላይ የካፍ ኢሌት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የሚታደሙ ይሆናል።