የኢትዮጵያ ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ከዛሬ 4:00 ጀምሮ እየተካሄዱ መሆኑ ይታወቃል።
በትናንትናው ዕለት የስፖርታዊ ጨዋነት ጉዳይ ላይ ዘላቂ መፍትሄ እስኪገኝ ድረስ በዚህ ዙር የሚደረጉ ጨዋታዎች ያለ ተመልካች በዝግ እንዲከናወኑ ውሳኔ መተላለፉን ማሳወቃችን ይታወሳል።
በመሆኑም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተደረገ ውይይት ጨዋታዎች በቅድመ ሁኔታ ለተመልካች ክፍት እንዲሆኑ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በዚህም መሠረት ተጋጣሚ ክለቦች ደጋፊዎቻቸው ስፖርታዊ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ ክለባቸውን እንዲደግፉ የማስተባበር ስራ እንዲሰሩ እና ክለቦችም ለስፖርታዊ ጨዋነት ቅድሚያ በመስጠት ሙሉ ኃላፊነት በመውሰድ ጨዋታዎች ለተመልካች ክፍት እንዲሆኑ፤ ፌዴሬሽኑም የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት በሚፈፅሙ ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ ውሳኔ ተላልፏል።