በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ከጥቅምት 20 – እስከ ጥቅምት 30/2014 በተካሄደው የምሥራቅና የሴካፋ ውድድር የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከአዘጋጇ ዩጋንዳ ጋር የመጨረሻ ጨዋታን ዛሬ በ9:30 ሰዓት የሚያደርግ ይሆናል። በአሰልጣኝ ፍሬው ሃይለገብርኤል እየተመራ የመጀመሪያ ጨዋታውን ጅቡቲን 7 ለ 0 ያሸነፈው የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛው ጨዋታው ኤርትራን 5 ለ 0 እንዲሁም ታንዛንያን 2ለ1 እና ብሩንዲን 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል። ታዳጊዎቹ ዋንጫውን ለማንሳት በነጥብ እኩል የሆነውን የዮጋንዳን ብሔራዊ ቡድን ማሸነፍ ዛሬ ይጠበቅባቸዋል።
በስድስት ሀገራት መካከል እየተካደ በነበረው የሴካፋ ሻምፒዮና ላይ የኢትዮጵያ ከ20 በታች ብሔራዊ ቡድን እና የአዘጋጇ ዩጋንዳ ቡድን ውድድሩ ያልተሸነፉ ሀገሮች ሲሆኑ ዩጋንዳ የተሻለ ስድስት የግብ ክፍያን ይዛ ምድቡን በቀዳሚ ስትመራ ኢትዮጵያ በእኩል ነጥብ ግብ ክፍያ ሁለተኛ በመሆን የመጨረሻው ጨዋታ አሸናፊው አገርን የሚለይ ይሆናል።