የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከቡና ባንክ ጋር የሦስት ዓመት የአጋርነት ስምምት መፈራረሙን ዛሬ በሞናርክ ፓርክ ቪው ሆቴል ይፋ ሆኗል።
ፌዴሬሽኑ ከባንኩ ጋር ከወራት በፊት የሦስት ዓመት ስምምነት በመፈፀም ሥራዎች ሲያከናወኑ የቆዩ መሆኑን የአጋርነት ስምምነቱ በተሰጠት መግለጫ ላይ ይፋ ተደርጓል።
በመግለጫው ላይ እንደተገለጸው ከሆነ ስምምነቱ ዋናውን የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ብቻ የሚመለከት ይሆናል። ይህም በየዓመቱ የሚታደስ ሲሆን ለ 3 አመታት የሚቆይ እና ለፌዴሬሽኑ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ የሚያስገኝ ሆኖ ከአንደ ደረጃ ስፖንሰሮች መካከል አንዱ ሆኗል:: በተጨማሪም በስምምነቱ በእያንዳንዱ የዋሊያዎቹ ጨዋታ ቡና ባንክ ለፌዴሬኑ 300 ሺህ ብር ክፍያም ይፈፅማል።