ዜናዎች

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኘሬዝዳንት ድሬዳዋ ስታዲዮምን ጎበኙ !

በዛሬው ዕለት ድሬዳዋ የገቡት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኘሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም የማስፋፊያ ግንባታ እና መጫወቻ ሜዳውን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፊራንኦል ቡልቻ የፌዴሬሽኑ ኘሬዝዳንት የተቀብሏቸው ሲሆን የስታዲየሙ ያለበትን ደረጃ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
በጎብኝታቸው የስታዲየሙን የተጫዋቾች መቀየሪያ የተገጠመውን እጅግ ዘመናዊ መቀመጫ ወንበሮቹ ተመልክተዋል።
በዚህ የመስክ ምልከታ ላይ ኮሚሽነር ፊራንኦል ቡልቻ ፣ የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ም/ኘሬዝዳንት አቶ ጉሌድ እና የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሰራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት ጨምሮ ዘመናዊ ሜዳውን ሰርቶ ያስረከበው አቶ ፎሀድ ኢብራሂም እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
No photo description available.
May be an image of 2 people, helicopter and text
May be an image of 5 people