ዜናዎች

የኢትዮጵያ እግር ኳስ የልዑካን ቡድን ነገ ወደ እስራኤል ያመራል! – ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ ታስቧል !

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የሚመራውና ፀሐፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን እንዲሁም ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የያዘው የልዑካን ቡድን ነገ ወደ እስራኤል እንደሚጓዙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በኢትዮጵያ እና በእስራኤል እግርኳስ ፌዴሬሽኖች መካከል ከረጅም ወራቶች በፊት ታስቦ በኮሮና ምክንያት ሳይሳካ የቀረው የሁለቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች የትብብር ስምምነቶችን በይፋ የማሳካት ሂደት እውን ለማድረግ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ነገ ወደ ቴላቪቭ የሚያመራ ይሆናል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአንድ ሳምንት የቴላቪቭ ቆይታው በታዳጊዎች ስልጠና እና ባለሙያዎች የልምድ ልውውጦች እንዲሁም አሰፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ለቀጣይ የሚረዳ መሠረታዊ ጅምር ስራዎች ያከናውናል ተብሎ ይጠበቃል።
ከቡድኑ ጋር አብሮ የሚጓዘው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከኮቪድ ጋር ችግሮች ካላጋጠሙት ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ ከእስራኤል ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያደርግ ይሆናል።የእስራኤል ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድንየ 2021/22 የአውሮፓ ከ 17 ዓመት በታች ሻምፒዮና ላይ ተካፋይ ሲሆን ሻምፒዮናውም በቅድመ ዝግጁ ላይ ይገኛል።

One thought on “የኢትዮጵያ እግር ኳስ የልዑካን ቡድን ነገ ወደ እስራኤል ያመራል! – ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ ታስቧል !

  1. በሰላም ተመለሱልን ውድ ልጆቻችን❤❤❤❤

    ፈጣሪ ስኬት ከፊታችሁ ያኑር

Comments are closed.