ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀዋሳ ከተማ የገንዘብ ቅጣት ተላልፎባቸዋል!

🕳በአምስተኛው ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ
👇
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ቅዳሜ ጥቅምት 24 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃግብር በተደረጉ ጨዋታዎች አምስት በመሸናነፍ ቀሪ ሶስቱ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል። 14 ጎሎች በ13 ተጫዋቾች ሲቆጠሩ ከግቦቹ 2 በፍፁም ቅጣት ምት እና 1 በራስ ላይ የተቆጠሩ ናቸው። 38 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ አንድ ቀይ ካርድ(በሁለተኛ ቢጫ) ተመዝግቧል ።
በተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች በተላለፈ ውሳኔ – ኦላኒ ሴቄታ(የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን መሪ) ማክሰኞ ጥቅምት 20 2016 ዓ.ም. ክለባቸው ከወልቂጤ ከተማ ጋር ባደረገው የ5ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ በ 77 ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀማቸው ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ ሲሆን የቡድን አመራሩ ለፈፀሙት ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 6000 /ስድስት ሺ/እንዲከፍሉ ወስኗል።
በክለቦች በተላለፈ ውሳኔ – ሃዋሳ ከተማ ከሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ5 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሃዋሳ ከተማ ቡድን አምስት ተጫዋች የሆኑት ሙጂብ ቃሲም ፣ መድሃኔ ብርሀኔ፣ በረከት ሳሙኤል፣ ማይክል ኦቱሉ እና እዮብ ዓለማየሁ በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ክለቡ የገንዘብ ቅጣት ብር 5000/አምስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል፡፡