ዜናዎች

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ከከባድ የመኪና አደጋ ተረፉ !

የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው
የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ከፍተኛ የመኪና አደጋ አጋጥሟቸው መትረፋቸው ተሰምቷል። በቅርቡ የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ በክለብ ደረጃ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ሻምፒዮ እና ኮከብ  አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ከሁለት ሳምንት በፊት እጅግ ከባድ የመኪና አደጋ አጋጥሟቸው መትረፋቸው ተሰምቷል። አሰልጣኝ ብርሃኑ አደጋው የደረሰባቸው ፍሬኑን የበጠሰ መኪና ቁልቁለት ላይ በሚወርድበት ጊዜ ከፊታቸው ሲመጣ እሱን አመልጣለው ብለው ወደ ግራ እግረኛ መንገድ በመታጠፍ መትረፋቸው ታውቋል።
ይሁንና ፍሬን የበጠሰው መኪና ከአሰልጣኝ ብርሃኑ ከኃላ የነበረው መኪና ላይ በመውጣቱ በመኪናው ውስጥ የነበሩ ት ሁሉም ህይወታቸው አልፏል።
አሰልጣኝ ብርሃኑ ለአራት ቀናት በግሩም ሆስፒታል ህክምና ተደርጎላቸው አሁን እቤታቸው የሚገኙ ሲሆን ከስፖርት ዞን ጋር ባደረጉት ቆይታም ከጓደኛው ጋር ሙሉ ለሙሉ መትረፋቸው እና መኪናቸው ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጪ መሆኑን ከዚህ ከባድ አደጋ ያተረፋቸውን አምላክን አመሥግነዋል።