ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች የ2013 ሊጎች እና ውድድሮች

-የኢትዮጵያ ቡና ክለብ በአራተኛው ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ አንድ መቶ ሺህ እንዲከፍል ተወስኗል !

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ ጥቅምት 18 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በሳምንቱ መርሃግብር በተደረጉ ጨዋታዎች አምስት በመሸናነፍ ቀሪ ሶስቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ በአጠቃላይ 19 ጎሎች በ16 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 27 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ አንድ ቀይ ካርድ(በሁለተኛ ቢጫ) ተመዝግቧል ።
በተጫዋቾች በረከት ወልደዮሐንስ(ሀዲያ ሆሳዕና) ክለቡ ከሀምበሪቾ ጋር ባደረገው የ4ኛ ጨዋታ በ50ኛ ደቂቃ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ተወስኗል።
በክለቦች ወልቂጤ ከተማ ፣ ሀዲያ ሆሳዕና እና አዳማ ከተማ በነበራቸው የ4ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ የክለቦቻቸው ደጋፊዎች የየእለቱ ዳኞችን አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦባቸው የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት ሶስቱም ከለቦች እያንዳንዳቸው ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።
ኢትዮጵያ ቡና ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር በነበረው የ4ኛ ሳምንት እግር ኳስ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱ ዳኞችን እና የተጋጣሚን ቡድን ተጫዋቾችን አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸውና የወንበር ስብርባሪ ወደሜዳ ስለመወርወራቸው ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የክለቡ ደጋፊዎች ከዚህ በፊት አፀያፊ ስደብ በመሳደብ ከተቀጡት ቅጣት ሊታረሙ ባለመቻላቸው በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ብር 75 000 /ሰባ አምስት ሺህ / እንዲሁም ቁሳቁስ ወደ ሜዳ በመወርውራቸው በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሠረት ብር 25 000 /ሀያ አምስት ሺህ / በድምሩ ክለቡ ብር 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።
በተጨማሪም ለኢትዮጵያ ቡና የቡድን መሪ እና የደጋፊ ማህበር ተወካይ የፕሪምየር ሊግ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ለማነጋገር ጥሪውን አስተላልፏል።