ዜናዎች

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ አካሄዷል!

 

የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማህበር ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በአራት ኪሎ ስፖርት ማዕከል (ወወክማ) አካሄዷል።

የስብሰባው አጀንዳዎች :-

-➖የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሪፖርት እና የኦዲት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሄዷል።
በተለይም በክለቡ ዓመታዊ ወጪ አጠቃላይ ዝርዝር የቀረበ ሲሆን በዋናነት ክለቡ ለተጨዋቾች በወር በደመወዝ ከ 3 ሚሊየን ብር በላይ በዓመት ደግሞ 45 ሚሊየን ብር ደሞዝ እንደሚከፍል ተብራርቷል።

በተመሳሳይ ክለቡ ለአሰልጣኞች በወር ለዋና አሰልጣኙ ከሶስት መቶ ሺህ ወይም ደግሞ በዓመት ከ 4 በሚሊየን ብር እና በአጠቃላይ ለሁሉም የቡድኑ ከ55 ሚሊየን ብር በዓመት ወጪ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
ከዚሁ ጋር በወጪነት በአሁኑ ሰዓት ቡድኑ የሀዋሳ ቆይታው ከ 2.5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በዚሁ ሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።

-➖ሌላው በክለቡ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የክለቡ የቦርድ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ፣ ስራ አስኪያጁ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ እና የክለቡ ደጋፊዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሰለሞን ታምራት ጨምሮ ከደጋፊዎች በተነሱ ጥያቄዎች እና የክለቡ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እና ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

በተለይም የክለቡ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ የክለቡን ስም በሚያገድፉ የስነምግባር ችግሮች በተባሉ ጉዳዮች ላይ ምላሽ ሰጥተዋል። በቅርቡ በክለቡ ስለ ተሰናበው ም/ አሰልጣኝ ዘላለም ጸጋዬ ጉዳይ ላይ በተነሱ ሃሳቦች ዙሪያ የክለቡን አቋም እና እውነታ ያሉትንም ጉዳይ የክለቡ ፕሬዝዳንት መቶ አለቃ ፈቃደ ይፋ አድርገዋል።

 

በተመሳሳይ ተጨዋቾች በዲሲፕሊን ጉድለት ዙሪያም ፕሬዝዳንቱ ምላሾችን ሰጥተዋል። በተለይም ከመጠጥ ጋር በተያያዘ የቡድኑን ስም የሚያበላሹ ተጨዋቾች ላይ ክለቡ በቀጣይም እርምጃ እንደሚወስድ ገልፀው ” ቡና የጀግና እንጂ የሰካራም ቤት አይደለም” በማለት በአፅኖት ተናግረዋል።

የስራ አመራር ቦርድ በተመለከተ ከደጋፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበው ምላሾች የተሰጡ ሲሆን የ2014 ዓ.ም. ዕቅድ ቀርቦ ፀድቋል።