አትሌቲክስ ዜናዎች

– በቶኪዮ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድኑ በመዝጊያው ስነስርዓት በባህል ልብስ በዛ ብሎ ታይተዋል ! – መቼ ይገባሉ ? አቀባበል ? እነማን ነበሩ? ከ250 ሚሊየን ብር በጀት ሆኗል ?

በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በመዝጊያ ሥነ ሥርዓት

 

የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በደማቅ የመዝጊያ ስነ-ስርአት ተጠናቋል። በ2020 የቶክዮ የመዝጊያ ስነ-ስርአት ሲጠናቀቅም በመክፈቻው ላይ ያልታየው  በመዝጊያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ  የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ  የልዑካን ቡድን በባህል ልብስ በስታዲየም ውስጥ በዛ ብሎ ታይል። 
ኢትዮዽያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ4 ስፖርቶች ያገኘችው 4 ሜዳሊያዎች ብቻ ነበር (1 ወርቅ ፤ 1 ብርና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎች) ከአፍሪካ 3ኛ ከዓለም 56ኛ ደረጃ አጠናቃለች። የልዑካን ቡድኑ ወደ ቶኪዮ የተጓዘው በ6 የተለያዮ ቀናት ሲሆን ዓላማው ምን እንደሆነ ግልፅ ባይሆንም በኦሎምፒክ ከተሳተፉት ከ38 አትሌቶች ቁጥሩ ባልተናነሰ ልዑክ ሆነው በጃፓን ለ20 ቀናት የሰነበቱበት ግን ቁጥራቸው በረከት ያለ ነበር ።
እንደውም ቀድመው የገቡት አብዛኛው አትሌቶች ሳይኋዮኑ የልዑካን ቡድን ሆነው የተጓዙት ባለስልጣናት ናቸወ።እነዚህ ሰዎች ደግሞ የሆቴልን የትራንስፖርት፣ የምግብ ወጪዎችን ተሸፍኖላቸው ከ 3 ሺህ ዶላር በላይ አበል በኪሳቸው አግኝተዋል። በአጠቃላይም ለልዑካን 250 ሚሊየን ብር በጀት ሆኗል
በአንፃሩ ተጠባቂዎቹ አትሌቶች የገቡት ውድድሩ 72 ሰዓታት ሲቀረው እንደነበር ይታወሳል። ይኸም የነበረውን ከባድ አየር ለመለማመድ አስቸጋሪ ሆኖባቸው ታይቷል።
የቶኪዮ ኦሊምፒክ ውድድሩ ተጠናቋል። ከ100 በላይ የሚሆነው የልዑካን ቡድኑም ምናልባትም በተናጠል ወይም ደግሞ የአውሮፕላን የደርሶ መልስ ትኬት በተቆጣጠረበት ቀን የፊታችን ዕረቡ ይገባሉ ተብሎ ሲጠበቅ  የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አቀባበልን አስመልክቶ ይፋ ያደረገው ነገር ባይኖርም ውጤት ላመጡ እና የሚቻላቸውን ላደረጉት አትሌቶች አቀባበል የሚኖር መሆኑ ተሰምቷል።
እነማን ነበሩ? 
ከአትሌቶቹ ፣ከአሰልጣኞቹ ፣ከቡድን መሪው ፣ የህክምና ባለሙያዎች እንዲሁም ከጋዜጠኞች ሆነው ከተጓዙት ውጪ እነማን ነበሩ ለሚለው ?
🔵 በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን
➖ ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ፕሬዝዳንት
➖ ዶ/ር በዛብህ ወልዴ ( ቡድን መሪ )
➖ አቶ አስፋው ዳኜ(ቴክኒክ ክፍል)
➖አቶ ቢልልኝ መቆያ(ፀሀፊ)
🔵በኦሎምፒክ ኮሚቴ
➖ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ(ፕሬዝዳንት)
➖ ኮማንደር ብርሀኔ አደሬ(ተ/ ም/ ፕሬዝዳንት)
➖ ወ/ሮ ኤደን አሸናፊ(ቡድን መሪ)
➖ አቶ ዳዊት አስፋው(ፀሀፊ)
➖ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ(ም/ ፀሀፊ )
🔵 የኦሎምፒክ ስራ አስፈፃሚዎች
➖ አቶ ወንድሙ ሀይሌ (ብስክሌት ፌዴሬሽን)
➖ አቶ ኢትዮጵያ በዴቻ ( ካራቴ ፌዴሬሽ)
➖ ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት(እጅ ኳስ ፌዴሬሽን)
➖አቶ ሚኒልክ ሀብቱ(.ቦውሊንግ አሶሴሽን)
➖አቶ ተሾመ ሶርሳ( ውሀ ስፖርቶች ፌዴሬሽን)
➖አቶ መስፍን አበራ(ቮሊቦል ፌዴሬሽን)
➖አቶ ሲሳይ ዮሀንስ(ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን)
➖ አቶ ጥላሁን ታደሰ(ክብደት ማንሳት ፌዴሬሽን)
➖ ወ/ሮ ሶፊያ አልማሙን(እግርኳስ ፌዴሬሽን)
🔵የመንግስትአመራሮች
➖ዶ/ር ሂሩት ካሰው( የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር)
➖ አቶ ኤሊያስ ሽኩር(ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር)
➖ አቶ ዱቤ ጂሎ(ስፖርት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር)
➖አቶ ባዘዘው ጫኔ (የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር )
➖ አቶ ዮናስ አረጋይ (የመአድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የፅህፈት ቤት ሀላፊ)
➖አቶ መስፍን ገ/ማሪያም(በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር) ሆነው ከስፓርት ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ጨምሮ ልዑካን ሆነው በቶኪዮ የሰነበቱ ነበር።
በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በመዝጊያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የልዑካን ቡድኑ በባህል ልብስ
ሰለሞን ባረጋ በ10 ሺህ የወርቅ ሜዳሊያ
ለተሠንበት ግደይ በ10 ሺህ የነሀስ ሜዳሊያ
ለሜቻ ግርማ # በ3 ሺህ መሠናክል የብር ሜዳሊያ
#ጉዳፍ ፀጋዬ በ5ሺህ የነሀስ ሜዳሊያ

One thought on “– በቶኪዮ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድኑ በመዝጊያው ስነስርዓት በባህል ልብስ በዛ ብሎ ታይተዋል ! – መቼ ይገባሉ ? አቀባበል ? እነማን ነበሩ? ከ250 ሚሊየን ብር በጀት ሆኗል ?

  1. ይህ ሁሉ የኢትዮጵያን ሀብት ለመቸብቻም እንጂ ፕረዚዳንት ፃፍ ምንም ጁንታ ሁላ

Comments are closed.