Sunday Mutuku
አፍሪካ ዜናዎች

“የኢትዮጵያ ሊግ ከአውሮፓው ሊግ ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ በኢትዮጵያ ሊግ መጫወቴ ለእኔ ትልቅ ኩራት ነው” – ኬኒያዊው ሰንደይ ሙቱኩ

ኬኒያዊው ሰንደይ ሙትኩ በመሃል ተከላካይና አማካኝ ስፍራ የሚጫዎት ሁለገብ ተጨዋች ነው። ተጨዋቹ በኢትዮዽያ ሊግ አምስት የውድድር ጊዜያት እና ለሶስት ክለቦች ተጫውቶ  አሳልፏል። ሰንደይ ሙትኩ ወደ ኢትዮዽያ ሊግ ከመምጣቱ በፊት በሀገሩ ኬኒያ እ.ኤ.አ 2015 ላይ ለ3ኛ ዲቪዚዮኑ ያታ ኮምቦይን እና ለ2ኛ ዲቪዚዮኑ ካካሜጋ ሆምቦይዝ ክለብ አምበል ሆኖ ተጫውቶል።   በኃላም ኤ.ኤ.አ 2017 ወደ ኢትዮጵያ ሊግ በመምጣት ለሲዳማ ቡና በመፈረም ከክለቡ ጋር የአንድ አመት ጥሩ ጊዜም አሳልፏል።

የተጨዋቹ የኳስ ክህሎትና ብስለት የተመለከቱት ሌሎች ክለቦችም በአመቱ ለማስፈረም ፍላጎት በማሳየታቸው ሰንደይ ሙትኩ ከሲዳማ በኃላ ድሬድዋ ከተማ  ማሳለፉ የሚታወስ ቢሆንም በአመቱ መጨረሻ  ድሬድዋ ከተማን መቀላቀሉ የሚታወስ ነው፡፡በዛው የውድድር ዓመትም የፋሲል ከተማ የክለቡ አመራሮች ቡድናቸውን ለማጠናከር በአፋጣኝ ተጨዋቹን አሰፍርመውም ነበር ።ሰንደይ ሙቱኩ ለፋሲል ከተማ የ1 አመት ኮንትራት ውል በኃላም እ.ኤ.አ 2019 የቀድሞ ክለቡን ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሎ አሁንም በሲዳማ ቡና ይገኛል። ኢትዮ ኪክ ከሰንደይ ሙትኩ ጋር ቆይታ አድርገናል እንሆ 

 

 

ኢትዮ ኪክ :- ከትላንት በስቲያ በነበረው ጨዋታ በፍፁም ቅጣት ምቱ በተቆጠረባችሁ ጎል በጣም አዝነህ ነበር ልበል ?
ሰንደይ :- አዎ። ግን ደግሞ ይሄ በእግርኳስ ውስጥ ያለ ኖርማል ነገር ነው። ለሙያው እና ለክለቡ ካለኝ ፍቅርና አክብሮት ስሜቱ ጎልቷል።
ኢትዮ ኪክ :- አንተ በነካኸው የእጅ ኳስ ፍፁም ቅጣት ተሸንፋችሁ ሦስት ነጥብ ማጣት የተለየ ስሜት አለው ?
ሰንደይ :- አዎ… መጥፎ ስሜት ይሰማል፤ … አሁን ግን ያን መጥፎ ስሜቱን ማሰላሰሉን ትቼ ለቀጣይ ጨዋታ እያሰብኩ ነው። ደግሞ እንዲህ ዓይነት አጋጣሚዎች ብዙ ጊዜ ታላላቅ ተጫዋቾችም እንዲሁ የሚያጋጥም ነው ፡፡
ኢትዮ ኪክ :- ከሲዳማ ቡና ጋር በዘንድሮው የውድድር ዓመት ምን ታስባለህ ?
ሰንደይ :- ሲዳማ ቡናን በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በሊጉ ውስጥ መሆኑን ማረጋገጥ እና የተሻለ ደረጃ ይዘን አመቱን እንድናጠናቅቅ እፈልጋለሁ።
ኢትዮ ኪክ :- ለዚህ ስኬት በግልህ እና በቡድንህ የምታደርገው ነገር ?
ሰንደይ :- ካለፉት ጨዋታዎች በተሻለ በቀጣይ ጨዋታዎች በግሌ ከፀሎት ጀምሮ እግዚአብሔር እንዲረዳን እለምናለሁ። በሜዳው ውስጥም በቀጣይ ጨዋታዎች ማድረግ የሚገባንን እናደርጋለን ብይ አስባለሁ።
ኢትዮ ኪክ :- በኢትዮጵያ ሊግ ውስጥ ፕሮፌሽናል ሆኖ መጫወትን እንዴት ነው የምትገልጸው ?
ሰንደይ :- በጣም ጥሩ. ነገር ። የኢትዮጵያ ሊግ  ከአውሮፓው ሊግ ጋር ስታንዳርዱ ተመሳሳይ በመሆኑ በኢትዮጵያ ሊግ መጫወቴ ለእኔ ትልቅ ኩራት ነው የሚሰማኝ።

ኢትዮ ኪክ :- አንተ ከአውሮፓ ያልክበት ነገር እንዳለ ሆኖ የኢትዮጵያን እግርኳስ ከምስራቅ አፍሪካ አገራት ጋር እንዴት ታነፃፅረዋለህ ?
ሰንደይ :- ምስራቅ አፍሪካ አገራት  ታንዛኒያ ቀዳሚ ፣ ኢትዮጵያዊ 2ኛ ፣ ዛምቢያ 3ኛ ኬንያ 4ኛ ይህ እንግዲህ በሁሉም የስፓርቱ አደረጃጀት ፣ አስተዳደር እና የተጨዋቾች ክፍያዎች እንዲሁም ሌልችን መስፈርቶች መሰረት ባደረገ መልኩ ማለቴ ነው
ኢትዮ ኪክ :- ስለዚህ በኢትዮጵያ ሊግ በመጫወት ደስተኛ ነህ?
ሰንደይ :- አዎ በጣም ።
ኢትዮ ኪክ :- በትኛው ክለብ የማይረሳ እና ጥሩ ጊዜ ያሳለፍከው ?
ሰንደይ :- ሲዳማ ቡና ከክለቡ ጋር ጥሩ ትዝታ አለኝ
ኢትዮ ኪክ :- ሰዎች ሙቱኩ የሚለውን ስምህ ሲሰሙ ኢትዮጵያዊ ትመስላቸኃለህ አጋጥሞህ ያውቃል ?
ሰንደይ :- አዎ ምን ስሜ ብቻ በአማርኛዬም ኢትዮጵያዊ የሚያደርጉኝ አሉ (በፈገግታ)
ኢትዮ ኪክ :- አማርኛ ትናገር ነበር እንዴ …በአማርኛ እንቀጥላ ?
ሰንደይ :- አዎ ይቻላል (በአማርኛ በፈገግታ)
ኢትዮ ኪክ :- ጥሩ ትናገራልህ ፣ ከቡድንህ ጋር በአማርኛ ነዋ የምትግባቡት ?
ሰንደይ :- አዎ( በፈገግታ) ደግሞ አንዴንዱ ሰው የአራዳ አማራኛ ይጨምራሉ እሱንም እችላለሁ (በፈገግታ)
ኢትዮ ኪክ :- ቤተሰቦችህ እዚህ ወይስ ኬንያ ?
ሰንደይ :- ባለትዳር እና የልጅ ወንድ አባት ነኝ ነህ ። ቆንጅዬ ባለቤቴ እና ወንድ ልጄ  ኬንያ ናችው።።
ኢትዮ ኪክ :-  የቀሪዎቹን የውድድር ዓመት ጨዋታዎች ምኞትህ?
ሰንደይ :- የእኔ ምኞት ከምወደው ክለቤ ጋር የዘንድሮ የውድድር ዓመቱን በጥሩ ደረጃ ማጠናቀቅ።
ኢትዮ ኪክ :- ስለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን
ሰንደይ :- እኔም አመሰግናለሁ !

 

One thought on ““የኢትዮጵያ ሊግ ከአውሮፓው ሊግ ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ በኢትዮጵያ ሊግ መጫወቴ ለእኔ ትልቅ ኩራት ነው” – ኬኒያዊው ሰንደይ ሙቱኩ

Comments are closed.