የአደይ አበባ ብሄራዊ ስታድየምን ግንባታ እያከናወነ የሚገኘው የቻይናው ተቋራጭ ባቀረበው የዋጋ ማስተካከያ ጥያቄ ላይ መግባባት ባለመቻሉ ከተቋራጪ ጋር የተገባው ውል እንዲቋረጥ መወሰኑን ሪፖርተር ዘግቧል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም በነበረው ውል ላይ 225 በመቶ የዋጋ ማስተካከያ በማድረግ 12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመክፈል ቢስማማም ኩባንያው 17 ቢሊዮን ብር እንዲከፈለው ሌላ የዋጋ ማስተካከያ ጥያቄ በማቅረቡ ውሉ እንዲፈርስ መደረጉን ዘገባው አክሏል።
በቴሌግራም :-
በኢንስታግራም ገጻችንን :-
ድረ ገጻችንን :-