በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በባህርዳር በተካሄደው የሴካፋ ከ 23 አመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ውድድር የብሄራዊ ቡድኑ ሁለተኛ አምበል የነበረው እና በዋናው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ልምምድ ላይ ጉዳት አጋጥሞት የነበረው ሀብታሙ ተከስተ ከጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ ማገገሙ ታውቋል።
በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አባል የሆነውና ከሁለት ሳምንት በፊት በልምምድ ሜዳ ከሌላው የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋች ጋር በደረሰ ንክኪ ጉዳት አጋጥሞት የነበረው አማካዮ ሀብታሙ ተከስተ ከጉዳቱ አግግሞ የፊታችን ሰኞ ልምምዱን እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል።
አሁን ያለበትን የጤንነቱን ሁኔታ በተመለከተ ሀብታሙ ተከስተ ለኢትዮኪክ ሲመልስ ” አሁን ክጉዳቴ እግዚአብሔር ይመስገን አገግሜያለው ፣ በጣም ደህና ነኝ። በቀጣይ ሳምንት ሰኞ ወደ ልምምድ የምመለስ ይሆናል ” በማለት ተናግሯል
ለኳታሩ 2022 የአለም ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታዎች በቀጣይ ከጋና እና ከዚምቧቡዌ አቻቸው ጋር የወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ ሌላኛውን የወዳጅነት ጨዋታ ከዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል። የዋልያዎቹ አማካኝ ሀብታሙ ተከስተ ቡድኑን ከጋና ጨዋታ በፊት የሚቀላቀል ሲሆን ሀብታሙ የፊታችን ሰኞ ከዓፄዎቹ ጋር ልምምዱን ይጀምራል።