ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” የአለም ፍፃሜ አይደለም ፣ ድክመቶች እና ጥንካሬዎችን እያየን ነው፣ አሁንም በጣም ጥሩ አቋም ላይ ነን ” አሰልጣኝ ፍራንክ ናታል

St. George Ethiopia Coach Frank Nuttall

 

እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ፍራንክ ናታል ከአዲሱ  ክለባቻው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለሶስተኛ ጊዜ  ጨዋታቸውን ዛሬ አድርገው የዛሬውን ጨዋታ በአቻ ውጤት ከጅማአባጅፋር ጋር አጠናቀዋል።   ከጨዋታ በኃላ ከሱፐር ስፓርት ቆይታ አድርገዋል።

በጨዋታው ደስተኛ አይመስሉም ?
” ሁሌም ጨዋታ ሲኖረን ቀደም ብዬም እንደተናገሩት ጨዋታ ሲኖረን የምንገባው አሸንፈን መውጣት ነው ። እናም የአለም ፍፃሜ አይደለም ፣ ደግሞም ጨዋታው ከባድም እንደሚሆን ጠብቀነው ነበር። ተጋጣሚያችን በሊጉ ለመቆየት ከመሆኑ አንፃር። ስለዚህ ይህን ጠብቀነው ነበር አንዳንዴ በዚህ መልኩ ሊያጋጥም ይችላል።
የአቻነቷን ጎል በተመለከተ ፈጣን ከመሆኗ አኳያ  አይተዋል ?
” አዎ አይቸዋለሁ… አዎ አይቸዋለሁ “
የትኩረት ማነስ ነው ጎሏ የተቆጠረባችሁ ማለት ይቻላል?
” …በእውነቱ ለመናገር ከጅማ ጥሩ ጎል እና ጥሩ አጀማመር የተቆጠረ ነበር “
ከቆሙ ኳሶች ነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጎሎች ያስቆጠረው ይሄ የማጥቂያ መንገዶት ነው ? 
” …ጨዋታዎቻችን ላይ የተለያዩ  ዕድሎችን ከክፍት ቦታዎች ስንጠቀም ነበር ። ወደ 16 የሚጠጉ ከክፍት ቦታዎች የተሞከሩ ኳሶች ነበሩ። ምናልባት ከቆመ ኳስ አንድ ቢሆን ይመስለኛል። ስለዚህ የተለያዪ ዕድሎችንም  የማጥቂያ መንገዶች እከተላለሁ። ነገር ግን ጎሎቹ በዛ የገቡት ።
የዛሬው ወጤት ቀጣይ ጨዋታዎች ላይ ተፅኖ ይኖረዋል?
” በፍጹም ምንም ተፅኖ የለውም። አሁንም ፉክክር ውስጥ እኮ ነን። ድክመቶች እና ጥንካሬዎችን እያየን ነው። አሁንም በጣም ጥሩ አቋም ላይ ነን።  ሌሎችም ቡድኖች ነጥብ ሲይዙና ነጥብል ሲጥሉ እያየን ነው።   ስለዚህ ይሄ ደግሞ በረጅም ጉዟችን ያለ ነው።