አትሌቲክስ ዜናዎች

የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ የምሽቱ ተጠባቂ የፍፄሜ ውድድር!

👇
በስኮትላንድ ግላስኮው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና እየተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተወዳደሩበት የማጣርያ ውድድር ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸው ይታወሳል።
በዛሬው ውጤት በ800ሜ የሴቶች ውድድር ግማሽ ፍፃሜ
ሀብታም አለሙ እና ፅጌ ዱጉማ ለፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
⭕የዛሬ ምሽቱ ተጠባቂ የፍፃሜ ውድድር
🕳ምሽት 5:15 ሰዓት የሴቶች 3000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ ኢትዮጵያዊያኑ ድንቅ አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋዬ፣ ሂሩት መሸሻ እና ለምለም ሃይሉ ተከታትለው በመግባት የሚያስችል ትልቅ ግምት ተሰጥቷቸው ።
:
🕳 በ 3000 ሜትር የወንዶች ፍፃሜ 5:40 ሰዓት ላይ ይካሄዳል። በዚህ ውድድር በጥሩ አቋም ላይ የሚገኘው አትሌት ሰለሞን ባረጋ እና ጌትነት ዋለ በተመሳሳይ የሚጠበቁ ይሆናል።