ቀጥታ ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

– የቤት ኪንግ ፕርሚየር ሊግ የ2014 የስፖርት ዞን ሽልማት ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት ሽልማት ተረክቧል !

የስፖርት ዞን የታሪክ አሻጋሪ የሆኑ ግለሰቦችን እውቅና ሲሰጥ ስድስት ግለሰቦችን ተሸላሚዎች አድርጓል።
በዚህም መሰረት :-
በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ የባህል እና ስፖርት ሚንስተር አቶ መስፍን ቸርነት ፣ የፌዴሬሽን ዋና ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ጨምሮ የስፖርቱ ቤተሰቦች በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
በመጀመሪያው የሽልማት ስነ-ስርዓት የአፍሪካን የነፃነት እግር ኳስ ያጀቡ አፓርታይድን በስፖርቱ የተዋጉት ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ የታሪክ አሻጋሪ ሽልማት ሲያሸንፉ ልጃቸው አማካኝነት በስፍራው ተረክቧል።
ከዚህ ባለፈም ከሐዋሳ ከተማ ጋር የመጀመሪያውን የሊግ ዋንጫ ያሳኩት እና በብሔራዊ ቡድን በረዳት አሰልጣኝነት የሰሩት አሰልጣኝ ከማል አህመድ ሌላኛው የታሪክ አሻጋሪ ተሸላሚ ሆነዋል።
ሶስተኛው የታሪክ አሻጋሪ ተሸላሚ የሆኑት በአትሌቲክሱ ዘርፍ እንደ ሀይለ ገ/ስላሴ ፣ ደራርቱ ቱሉ እና ብርሀኔ ሀደሬ የመሳሰሉ ሯጮችን ለሀገሪቱ ያበረከቱት ዶ/ር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ተሸልመዋል።
ዶ/ር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ሀገራቸውን በአምስት ኦሎምፒክ ሲመሩ ሀያ ስምንት ሜዳሊያዎችን ሲያስገኙ የስፖርት ዞን የታሪክ አሻጋሪ ተሸላሚ ሲሆኑ በህይወት ባይኖሩም ልጃቸው ያቆብ ኮስትሬ በስፍራው የአባቱን ሽልማት ተረክቧል።
በአራተኛ የታሪክ አሻጋሪ ሽልማት አሸናፊ ዘርፍ ጋዜጠኛ እና የእግር ኳስ ታሪኮችን ሰንዶ ያዘጋጀው ገነነ መኩሪያ ተሸላሚ ሆኗል።
በአምስተኛው የታሪክ አሻጋሪ የህይወት ዘመን ሽልማት በአትኬቲክሱ ዘርፍ በኦሎምፒኩ የሀገሩን ባንዲራ ያውለበለበው ምርፅ ይፍጠር ሲሸለም ልጁ ቢንያም ምርፅ በስፍራው በመገኘት ሽልማቱን ወስዷል
–የአመቱ  ስድስት ተሸላሚዎች !
1. የ 2014ዓ.ም የስፖርት ዞን የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች በአሁን ሰዓት ይፋ ሲደረግ በሐዋሳ ከተማ የውድድር ዘመኑን ያሳለፈው ብሩክ በየነ አሸናፊ ሆኗል።የኢትዮጵያ ከ 23ዓመት በታች ዋና አሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ ለአሸናፊው ብሩክ በየነ ሽልማቱን አበርክተዋል።
2- የ 2014ዓ.ም የስፖርት ዞን የአመቱ ምርጥ ምስጉን ዳኛ ዘርፍ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ዶ/ር ሀይለየሱስ ባዘዘው በኮከብ ዳኝነት አሸናፊ ሆኗል
3- የ 2014 የስፖርት ዞን የአመቱ ግብ ጠባቂ በመባል ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግን ያሸነፈው ቻርለስ ሉክዋጊ በአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል።
4. የ 2014 የስፖርት ዞን የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በመባል ቅዱስ ጊዮርጊስ የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሻምፒዮን ያደረገው አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ በአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል።
5- የ 2014 የአመቱ ምርጥ ደጋፊ ዘርፍ የባህር ዳር ከነማ ደጋፊዎች አሸናፊ ሆነዋል።
6- የ 2014 የስፖርት ዞን የአመቱ ምርጥ ተጫዋች በመባል ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግን ያሸነፈው ጋቶች ፓኖም በአመቱ ምርጥ ተጫዋች ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል።