ዜናዎች

የቤት ኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በምሽት እንዲደረጉ ማሻሽያ ተደረገ !

የ2013 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በኮቪድ ምክንያት በተመረጡ አምስት ከተሞች እየተካሄ ይገኛል። አራተኛዋ የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አስተናጋጅ ከተማ ድሬዳዋም   ከነገ ጀምሮ  ከ17ኛው ሳምንት እስከ 21ኛው ሳምንት ያሉትን ውድድሮች የምታስተናግደ ይሆናል።   በውድድሩ ተሳታፊ ክለቦች በደማቅ አቀባበል ድሬደዋ ገብተዋል ። ታሪካዊው የድሬዳዋ ስታዲየም ለመጀመሪያ ጊዜ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግን በምሽት  እንደሚደረጉ ተረጋግጧል ።ከዚህ በፊት በስራ ሰዓት ይደረጉ የነበሩ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ ለቀጣይ ሳምንታት በምሽት የሚካሄዱ ይሆናል ። በዚህ መሠረት ከረቡዕ መጋቢት 29 ጀምሮ ቀን 10:00 ሰዓትና ምሽት 1:00 ሰዓት ጨዋታዎቹ እንደሚካሄዱ የውድድሩ አዘጋጆች አሳውቀዋል።