ዜናዎች

” የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በኮሮና ምክንያት ሊቋረጥ ይችላል ” -፻ አለቃ ፈቃደ ማሞ

በኢንተርኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል አሁን እየተካሄደ በሚገኘው የውድድር አመቱ የ16 ሳምንታት ጨዋታዎች ግምገማ እና ውይይት ላይ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትን ጨምሮ፡ ከ13ቱ የሊጉ ባለ አክሲዮን ክለቦች የ10ሩ አመራሮች ፣ስራ አስኪያጅ፣ ቡድን መሪ ወይም አሰልጣኞች ተገኝተዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ የሊግ ኮሚቴው ውድድሩን የመራበት ሂደት አድናቆት የሚገባው ነው ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም፡ በሊጉ ዳኝነት ላይ መሻሻሎችን ለማምጣት ተጠሪነቱ ለፌዴሬሽኑ የሆነውን የዳኝነት ኮሚቴ አመራሮችን መቀየሩንም አስታውቀዋል።
የሊግ ኮሚቴው የቦርድ ፕሬዝዳንት የ፻ አለቃ ፈቃደ ማሞ ፉክክሩ በቀጣይ የሚካሄድባቸው ሀዋሳ እና ድሬዳዋ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ቀዳሚዎቹ አካባቢዎች መሆናቸውን በማስታወስ፡ ውድድሩ በወረርሽኙ ምክንያት እንዳይቋረጥ ክለቦቻችን ትልቅ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። የ፻ አለቃ ፈቃደ ማሞ እንደተናገሩት ” ሊጉ በቀጣይ የሚደረግባቸው ከተሞች ድሬደዋ እና ሀዋሳ በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅታዊ የኮቪድ ቫይረስ ከፍተኛ ቁጥር የሚያስመዘግቡ ከተሞች መሆናቸውን አሳስበው ክለቦች ተጫዋቾቻቸውን ከሆቴል በሻይ እና በሽርሽር ብለው መውጣት መከልከል እንዳለባቸው አለበለዚያ በኮሮና ስርጭት ምክንያት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሊቋረጥ ይችላል ” በማለት አሳስበዋለው ።
@ልዪ ስፖርት