ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት የዲስፕሊን ውሳኔዎች!

 

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በድሬዳዋ የሚያደርገውን የስድስት ሳምንት ጨዋታዎች ቆይታ ካሳለፍነው አርብ መጀመሩ ይታወቃል ። ከዚሁ ቀን ጀምሮም ለተከታታይ አራት ቀናት የ10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተካሂደው በነዚህ 8 ጨዋታዎች 30 የማስጠንቀቂያ የቢጫ ካርዶችን ተጫዋቾች እና የቡድን አመራሮች የተመለከቱ ሲሆን ምንም አይነት የቀይ ካርድ አልታየም ።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ማክሰኞ ጥር 24 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ተጫዋቾች :-
ከስር ስማቸው የተዘረዘሩ ተጫዋቾች 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከቱ በመሆናቸው እያንዳንዳቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱ እና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።
1. ፍሬዘር ካሳ(ሀዲያ ሆሳዕና)
2. አናጋው ባደግ(ወላይታ ድቻ)
3. ዊሊያም ሰለሞን(ኢትዮጵያ ቡና)

ክለቦች :-
ጅማ አባ ጅፋር እግርኳስ ክለብ ክለቡ እሁድ ጥር 22 2014 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ከተማ ባደረገው የ10ኛ ሳምንት መርሃግብር ጨዋታው 5/አምስት/ ደቂቃ ዘግይቶ አንዲጀመር ምክኒያት ስለመሆኑ ከጨዋታ ታዛቢ ሪፖርት ስለቀረበበት ክለቡ ለፈፀመው ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

የኮቪድ የምርመራ ውጤት :-
በአንድ ማዕከል የኮቪድ ምርመራ ለተጫዋቾች፣ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት እና ዳኞች ተደርጓል። በሳምንቱ አጠቃላይ 561 ምርመራ ተደርጎ የተገኘ ፖዘቲቨ ውጤት የለም።