ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ በሁለት ቀን ጨዋታዎች አስር ጎሎች ተቆጥረዋል

የ14ኛው ሳምንት የሁለተኛ ዙር የሁለተኛው ቀን የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሁለት ቀን አስር ጨዋታዎች ተቆጥረዋል።አስገራሚ የቤትኪንግ ውጤቶች የተሰተናገዱበት የዛሬው ጨዋታ ረፋድ ላይ አዳማ ከተማ ጅማ አባጅፋርን ሁለት ለአንድ እንዲሁም የከሰአቱን ጨዋታ ደግሞ ወላይታ ድቻ ሀዲያ ሆሳዕናን ሁለት ለባዶ አሸንፈው ለዋንጫ ፍክክር የሚጓዙትን ሀዲያን አስደንግጠዋል።የሁለተኛ ዙር የ14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገም የሚካሄዱ ሲሆን ረፋድ ላይ ወልቂጤ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ከሰአት ደግሞ ሲዳማ ቡና ከባህርዳር ከተማ ይጫወታሉ።