ዜናዎች

የቤትኪንግ ጨዋታዎች በቀጣይ በምሽት ለማካሄድ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ግዢ ተፈፅሟል !

የ2013 የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ውድድር የኮቬድ ፕሮቶኮልን መሰረት በተመረጡ አምስት ከተሞች ውድድር ለማድረግ በታቀደው መሰረት በሶስቱ ከተሞች ውድድሩ መደረጉ ይታወሳል። በቀጣይም ድሬዳዋ ውድድሩን ከመጋቢት 27-ሚያዚያ 15/2013 ዓ.ም ለማድረግ ዝግጅቷን አጠናክራለች። የቤትኪንግ ጨዋታዎች በቀጣይ የአየር ንብረቱ ሞቃታማ በሆነችው ድሬ መካሄዱን ተከትሎ ውድድሩን ከ11: 00 እስከ ምሽት ለማካሄድና ሜዳውም በምሽት እግር ኳስ ማጫወት የሚያስችል የመብራት አገልግሎት እንዲኖረው በተጠየቀው መሰረት ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ጥያቄውን አሳክቷል። የቤትኪንግ ጨዋታዎች በምሽት ለማካሄድ በናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር 766 ኪ.ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል በብር 2,454,651 (ሁለት ሚሊየን አራት መቶ ሀምሳ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሀምሳ አንድ ብር የፈጀ የትራንስፎርመር ግዢ ተፈፅሞለታል