ቀጥታ ዜናዎች

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 1ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነስርዓት ኮሚቴ ዛሬ መስከረም 24/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በተጫዋቾች ኤልያስ አህመድ(ድሬደዋ ከተማ) ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳድብ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ስለመሆኑ ሪፖርት የቀረበበት ሲሆን ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 3 ጨዋታ እንዲታገድና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል እንዲሁም ጊት ጋትኩት(ሲዳማ ቡና) ፣ ሽመክት ጉግሳ(ፋሲል ከነማ) ፣ ዊሊያም ሰለሞን(አዳማ ከተማ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀም ቀይ ካርድ አይተው ከጨዋታ ሜዳ የተወገዱ 1 ጨዋታ እንዲታገዱ፥ እንየው ካሳሁን(ድሬዳዋ ከተማ) ሃይማኖታዊ መልእክት የሚያስተላልፍ ምስል በውስጥ ልብሱ ደርቦ ስለመልበሱ ሪፖርት የተደረገበት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ተጫዋቹ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ እንዲሁም ክለቡ ብር 10000 /አስር ሺህ ብር/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

 

በክለብ ደረጃ ድሬደዋ ከተማ በሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ አምስት ተጫዋቾች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ፣ ኢትዮጵያ መድን ባደረገው ጨዋታ ከዕረፍት መልስ የክለቡ ተጫዋቾች 4 ደቂቃ ወደሜዳ ዘግይተው ስለመግባታቸው ሪፖርት የተደረገበት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ ክፍል መሰረት ክለቡ የገንዘብ ቅጣት ብር 15000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ እንዲከፍል እንዲሁም በዚህ ምክኒያት የቀጥታ ቴሌቭዥን ስርጭት መብት የገዛው ድርጅት የአክሲዮን ማህበሩን የካሳ ክፍያ ከጠየቀ የተጠየቀውን ክፍያ እንዲከፍል ፣ ወልቂጤ ከተማ ባደረገው የሳምንቱ ጨዋታ የክለቡ ተጫዋች ሳሙኤል አስፈሪ ከተፈቀደው የመለያ ቁጥር/1-50/ ውጪ 66 ቁጥር ለብሶ ስለመጫወቱ ሪፖርት የተደረገበት በመሆኑ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ክለቡ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ እንዲከፍል ተወስኗል፡

One thought on “የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 1ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች!

Comments are closed.