የቤትኪንግ ኢትዮጵያ የ10ኛ ሳምንት የዲስፕሊን ውሳኔዎች ተሰጥተዋል!

የ10ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2014 በድሬደዋ ስታዲየም ከጥር 20 እስከ ጥር 23/2014 ዓ.ም በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል። በተደረጉ ስምንት ጨዋታዎች ሰባት ጨዋታዎች በመሸናነፍ አንድ ጨዋታ በአቻ ሲጠናቀቅ 19 ግቦች በ17 ተጫዋቾች ተመዝግበዋል። 30 በቢጫ ካርድ የተገሰፁ ተጫዋቾችና የቡድን አመራሮች ሲሆኑ የታየ ቀይ ካርድ የለም። ውጤት ማፅደቅን ተከትሎ ከፀጥታውም ሆነ ከዳኝነት አንፃር ውጤታማ ሳምንት መሆኑ በሊጉ ውድድርና ስነስርዓት ኮሜቴ ዛሬ ተገምግሟል።

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች:

በሳምንቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ማክሰኞ ጥር 24 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች) ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በተጫዋቾች :-

ፍሬዘር ካሳ(ሀዲያ ሆሳዕና) ፣ አናጋው ባደግ(ወላይታ ድቻ) እና ዊሊያም ሰለሞን(ኢትዮጵያ ቡና) 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክተዋል።

-በመሆኑም ተጫዋቾቹ እያንዳንዳቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

በክለብ :-

ደረጃ ጅማ አባ ጅፋር እግርኳስ ክለብ ክለቡ እሁድ ጥር 22 2014 ዓ ም ከአዲስ አበባ ከተማ ባደረገው የ10 ኛ ሳምንት መርሃግብር ጨዋታው 5/አምስት/ ደቂቃ ዘግይቶ አንዲጀመር ምክኒያት ስለመሆኑ ከጨዋታ ታዛቢ ሪፖርት ስለቀረበበት ክለቡ ለፈፀመው ጥፋት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።

የኮቪድ የምርመራ ውጤት:-

በአንድ ማዕከል የኮቪድ ምርመራ ለተጫዋቾች፣ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት እና ዳኞች ተደርጓል። በሳምንቱ አጠቃላይ 561 ምርመራ ተደርጎ የተገኘ ፓዘቲቨ ውጤት የለም።