ዜናዎች

የባህርዳሩ የሴካፋ ዋንጫ ተካፋይ ዮጋንዳ ሁለተኛውን የወዳጅነት ጨዋታ ከሳውዲ አረቢያ ጋር ዛሬ ያደርጋል !

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ሐምሌ 10/2013 እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያስታወቀው ከ23 ዓመት በታች የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ላይ ተካፋይ የሆነው የዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን አቋማን በወዳጅነት ጨዋታ እያጠናከረ ይገኛል። በምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ጠንካራ ቡድንና በተደጋጋሚ ሻምፒዮና የሆነው የዮጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ባለፈው ሳምንት ሳውዲ አረቢያ የተጓዘ ሲሆን ባለፈው ዓርብ የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታውን ከሳውዲ አረቢያ ከ23 ዓመት በታች ጋር አድርጓል። በውጤቱም ሁለቱም ሀገራት ያለግብ 0 ለ 0 በአቻ ውጤት አጠናቀዋል።
የዮጋንዳ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን  በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ለሚጀምረው የሴካፋ ውድድር ሁለተኛውን የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን  ዛሬ ምሽት ከሳውዲ አረቢያ ጋር የሚያደርግ ሲሆን ከጨዋታው በኋላ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ከቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞውን የሚያደርግ ይሆናል።