ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” የቡና ደጋፊ በስታዲየሙ ቢኖር በራሱ አንድ ደስታ ነበር: የእኔ ሪከርድ ተሳክቷል፤ የክለቤ ውጤት ፣ አልተሳካም በጣም አዝኛለሁ “- አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና )

አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና )

ኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች አቡበከር ናስር በአንድ የውድድር ዘመን በርካታ ጎል በማስቆጠር ሪከርድን ሰብሯል፡፡ በዛሬው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ላይ 9ኛ ፣ 36ኛው ፣90 ደቂቃ ሶስት ጎሎችን አስቆጥሮ የውድድር ዘመን ጎሎቹን ቁጥር 2ት አድርሷል፡፡ አቡበከር ናሰር በዛሬው ጨዋታ አራተኛ ጊዜ ሃትሪክ ከመያዙ በተጨማሪም በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሲዳማ ቡና ላይ ሁለተኛውን ሀትሪክ በመያዝ ሌላ ተጨማሪ ሪከርድ ይዞም ወጥቷል። አቡበከር ናስር በምርጥ ብቃት የጎ አግቢነት ሪከርዱን በእጁ ከማስገባቱ በተጨማሪም በቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች ጎል የሚያስቆጥር ከሆነ በቀላሉ የማይደፈር ሪከርድ ጨብጦ የውድድር ዓመቱን በኮከብነት ያጠናቅቃል ማለት ነው

አቡበከር ናስር ከሱፐር ስፓርት ጋር ያላደረገውን ቆይታ እንሆ :-

በቅድሚያ እንኳን ደስ ያለህ
” እንኳን አብሮ ደስ አለን”
ከጨዋታው በፊት በዛሬው ጨዋታ ሶስት ጎሎች አስቆጥራለሁ ብሎ ስማሰቡ ?
” አይ እኔ ሶስት አገባለሁ ብዬ አላሰብኩም። ግን የተሸለ ነገር ቡድኔ እንዲያገኝ ለማድረግ ነበረ ያሰብነው። ከትናንት ጀምሮ ከቡድኔ ልጆች እና ከአሰልኞቹ ጋር ጥሩ ምክክር አድርገን ነበር። እላህ አላለውም አልተሳካም።
አምበል ሆኖ ነበር በዛሬው ጨዋታ የገባው ፣ አምበል መሆኑ የተለየ ስሜት ሰለመኖሩ?
“ያው ኢትዮጵያ ቡናን በአምበልነት ስትመራ በጣም ትልቅ ስሜት ነው የሚሰማው። ምክንያቱም ገና በልጅነቴ ይሆን ክብር ላሳየኝ ክለቡንም ደጋፊውንም ማመሥገን እፈልጋለሁ። በየትኛውም አካባቢ ስሄድ ሁለም የስፓርት ቤተሰብ ድጋፍ እያደረጉል ነውና ሁሉንም ማመስገን እፈልጋለሁ።
ሪከርዱን ሲሰብር ደጋፊዎች በስታዲየም ቢኖሮ ብሎ ቁጭት ስለማደሩ ?
” አዎ! በሚገባ ። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ በስታዲየሙ ቢኖር ከ30 ሺህ ህዝብ በላይ ነበር እየገባ የሚያውና በእነሱ ታጅቦ መጫወት በራሱ አንድ ደስታ ነበር እና ፣ ይህ ነገር ደግሞ አልተሳካም። አንድ ቀን ይሳካል። ለቀጣይ ዓመትም ደግሞ ያው ኮቪድ ጠፍቶ በጋራ ሆነን ኳሳችንን እንድናካሄድ የማስበው”
በአንደኛ ዙር ሲዳማ ቡና ላይ ሃትሪክ መስራቱ እና አሁንም ሲዳማ ቡና ላይ ሃትሪክ መስራቱ የተለየ ነገር ካለው ?
” የተለየ ነገር የለውም። በየጨዋታው የተሻለ ነገር ለማድረግ ነው የምገባው እና ያ ነገር ሜዳ ላይ እኔ ትኩረት አድርጌ ነው የሚጫወተው። አንደኛ የራሴን ራከርድ ለመስበር ነው የምጫወተው ፣ ሲቀጥል ደግሞ ክለቤም ውጤት እንዲይዝ ነውና። የእኔ ሪከርድ ተሳክቷል የክለቤ ውጤት ፣አልተሳካም፣ በጣም አዝኛለሁ ።
በትላንቱ የብሔራዊ ቡድኑ የሽልማት ስነስርዓት ላይ ከጌታነህ ጋር ነበሩ እና ያወሩት ነገር ስለመኖሩ ?
” ትላንትና ከእነሱም ጋር ተገናኝተን ነበረ። ለዛውም ስለመሸ ነገ ጨዋታ አለብህ ሂድ ብሎኝ ቸበር። ጌታነህ እና ዮርዳኖሰን ማመስገን እፈልጋለሁ። ሁለቱም እያበረታቱኝ ነው። እንዲሁም የስፓርት አፍቃሪዎች ፣የሌላም ክለብ አሰልጣኞች እና ብዙ ሰዎች እየደወሉ እያበረታቱኝ ነው ። ለእነሱ ምስጋና ለማቅረብ እፈልጋለሁ።
በአራት ሃትሪኮች የወሰዳቸውን ኳሶች ምን ለማድረግ እንዳሰበ ?
” በፈገግታ ገና ላስብበት በፈገግታ