ዜናዎች

የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ አዲሱ እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ቅዳሜ ይገባል !

ከደቡብ አፍራካዊው ማሂየር ዴቪድስ የተለያየው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አዲስ አሰልጣኝ ሊቀጥር እንደሆነ ለጉዳዮ ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ለኢትዮ ኪክ አድርሰዋል።ከጀርመናዊው ኤርነስት ሚድንዶርፕ ጋር ከተለያየ በኃላ ምክትሉን የ34 አመቱን ማሂየር ዴቪድስ በጊዜያዊ አሰልጣኝ አድርገው ከሾሙ በኃላ ከአሰልጣኙ ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ የአዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ቅድመ ሰምምንቶች  መደረጋችውን  ዛሬ ተሠምቷል።የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ዛሬ ማለዳ ቢሾፍቱ በሚገኘው የይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ የወዳጅነት ጨዋታ ከሲዳማ ቡና ጋር ካደረገ በኃላ የክለቡ ዋና ኃላዎች ቀጣዮን የአዲስ አሰልጣኝ በተመለከተ መረጃውን ለሚመለከታቸው የክለቡ አባላት አካፍለዋል።
በመረጃው መሠረት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አዲሱ ቀጣይ አሰልጣኝ እንግሊዛዊ መሆናቸው ሲሰማ አዲሱ አሰልጣኝ የፊታችን ቅዳሜ አዲስ አበባ እንደሚመጡ እና ከእንግሊዛዊ አሰልጣኝ ጋር ስምምነት እንደሚጠናቀቅም  የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። ፈረሰኞቹ ከአዲሱ እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ቅጥር  ከተካሄደ በኋላም አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ በምክትል አሰልጣኝነት የሚቀጥል እንደሆነም መረጃው አያይዞ ጠቁመዋል። ፈረሰኞቹ ቢሾፍቱ በሚገኘው የይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ የወዳጅነት ጨዋታ ዛሬ ረፋድ ከሲዳማ ቡና ጋር አድርግው  በ2 ለ 2 አቻ ውጤት ሲያጠናቅቁቭ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል ሳልሀዲን ሰኢድ እና አቤል ያለው ጎሎቹን አስቆጥረዋል ።
እንደሚታወሰው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ባለፉት በ18 ዓመታት ውስጥ ቀጥራቸው 17 የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸውን አሰልጣኞች የቀጠረ ሲሆን በዘንድሮው የውድርር አመት በአራት ወራት ውስጥ ሁለት የውጭ አሰልጣኞችን በመቀየር ፈጣን  የውጭ ሀገር የአሰልጣኝ ለውጥ አድርጓል።ቅዱስ ጊዮርጋስ ክለብ የፊታችን ቅዳሜ ከእንግሊዛዊ አሰልጣኝ ጋር ስምምነቱን ከፈፀመ ደግሞ  በ18 ዓመታት ውስጥ 18ኛውን   የውጭ ዜግነት ያለቻው አሰልጣኝ በመቅጠር በአገሪቱ ክለቦች ቀዳሚ ይሆናል።።