ዜናዎች

ቅዱስ ጊዮርጊስ አምበሉን ጨምሮ አራት ወሳኝ ተጫዋቾቹን አገደ ! – ተጫዋቾቹ አዲስ አበባ እንዲመለሱም ተወሰነ!

የቅዱስ ጊዮርስ ስፖርት ማህበር በ2013 ዓ.ም በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እየተሳተፈ የሚገኘው እንደሆነ ይታወቃል።
ቡድኑ በትላንትናው የቤትኪንግ አቻ ውጤት ማጠናቀቁም አይዘነጋም። ክለቡ ዛሬ እንዳሳወቀው ከሆነ ቡድኑ አሁን ላይ ውጤት አርኪ የሚባል እንቅስቃሴዎችን እያደረገ አለመሆኑ አሳውቆ አልፎ አልፎ በቡድኑ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ተጫዋቾቻችን የሚያሳዩት ያልተገባ ባህሪና የስነ-ምግባር ጉድለት እጅጉን የሚያስቆጭ እንደሆነ አሳውቋል።
ትናንት ቡድኑ በድሬዳዋ ስታዲየም ከጅማ አባጅፋር ጋር ካካሄደው የ20ኛ ሳምንት ጨዋታ በኃላ ጌታነህ ከበደ፣ አስቻለው ታመነ፣ ጋዲሳ መብራቴ እና ሙሉዓለም መስፍን ከፍተኛ የዲሲፒሊን ግድፈት ፈጽመዋል፡፡
አብዛኞቹ ተጫዋቾች ከዚህ ቀደም ቡድኑ በባህርዳር በነበረው ቆይታም የስነ ምግባር ጉድለት ፈጽመው የነበረ ቢሆንም አጠቃላይ ለቡድኑ ውጤታማነትና አንድነት ሲባል በማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ተደርጎ ነበር፡፡የክለቡ ስራ አመራር ቦርድ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ተጫዋቾቹ በፈጸሟቸው የዲስፕሊን ግድፈቶች ዙሪያ የቡድን መሪው በተፈጸመው የሥነ ምግባር ጉድለት ዙሪያ በዝርዝር በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ ቦርዱ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ለጊዜው ከቡድኑ ታግደው እንዲቆዩ ተወስኗል፡፡
ስለሆነም አራቱም ተጫዋቾች ከድሬዳዋ በዛሬው እለት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ መደረጉን ክለቡ አሳውቋል