አፍሪካ ዜናዎች

# የቅዱሱ ጊዮርጊሱ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ወደ ደቡብ አፍሪካው ስዋሎስ ኤፍ ሲ በቀጣዪቹ ቀናት ያቀናል !

Amanuel Gebremichael

 

የቅዱስ ጊዮርጊሱ የፊት መስመር ተጫዋች እና የዘንድሮውን የውድድር ዓመት ጉዳቶችን አስተናግዶ የነበረው አማኑኤል ገ/ሚካኤል በቀጣዮቹ ቀናት ወደ በደቡብ አፍሪካ እንደሚጓዝ ተረጋግጧል።

ከወራቶች በፊት ከደቡብ አፍሪካ ትልልቅ ክለቦች ጋር ስሙ ሲነሳ የነበረው አማኑኤል ገ/ሚካኤል አሁን ላይ በምን በኩል እንደሆነ ሳይታወቅ ከደቡብ አፍሪካው የሶዌቶ ከተማ ክለብ ከሆነው ስዋሎስ ኤፍ ሲ ጋር የሙክራ ጊዜ ለማድረግ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚጓዝ ኢትዮኪክ ማረጋገጥ ችላለቸ።

በዚህ መሠረት አማኑኤል የደቡብ አፍሪካ ቪዛ እና መሠል ጉዳዪች መጨረሱ ሲታወቅ ክለቡ የቅድመ ዝግጅት ሲጀምር እና ሲያሳውቁት ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚጓዝ ታውቋል።

የደቡብ አፍሪካው ስዋሎስ ኤፍ ሲ በተጠናቀቀው የደቡብ አፍሪካ ፕሪሚየር ሺፕ 8ኛ ሆኖ መጨረሱ ሲታወቅ ክለቡ ዋና አሰልጣኙን ማሰናበቱን ተከትሎ አሁን ላይ በቅርቡ የተጨዋችን ዘመኑን ያጠናቀቀው የቀደሞ ተጨዋች አሰልጣኝ ሆኖ ቡድናኑን እንደሚያሰለጥን ታውቋል።