ፖርቱጋላዊው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የጋና ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት ማሪያኖ ባራቶን የጋናው አሣንቴ ኮቶኮ ክለብ አዲስ አሰልጣኝ ሆነዋል።የጋናው ክለብ ከወራቶች በፊት ማክስዌል ኮናዱን ካሰናበተ በኃላ ፖርቱጋላዊውን ማሪያኖ ባራቶ በቦታው መተካቱ ሲሰማ አሰልጣኙም ወደ ጋና መድረሳቸው ታውቋል ፡፡ፖርቱጋላዊው ማርያኖ ባሬቶ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የዋና የአሰልጣኝነት ፈቃድ ከማግኘታቸው በፊት በረዳት አሰልጣኝነት ዳይናሞ ሞስኮ ፣ የዱባዩን አልናስር ክለብ እና በተለያዪ ክለቦች አሰልጥነዋል። በኃላም ፖርቱጋላዊው አሠልጣኝ ማርያኖ የጋናን ብሄራዊ ቡድን እንዲሁም እ.ኤ.አ ከ2014 እስከ – 2015 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በ15 ሺህ ዶላር ወርሀዊ ክፍያ የዋልያዎች ዋና አሰልጣኝነት ሆነው መሰራታቸው ይታወሳል።