ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ የ2013 ሊጎች እና ውድድሮች

#የሸገር ደርቢን እና በታላቁ የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት አስመልክቶ ፈረሰኞቹ የቀን ለውጡን ዛሬ ይፋ አድርገዋል!

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር 87 ኛ አመት የምስረታ በዓሉን በታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት ለማክበር ቀደም ብሎ ፕሮግራም መያዙ ይታወቃል። በአንፃሩ በርካታ ተጨዋቾችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ በድን ያስመረጡት ፈረሰኞቹ ተጫዋቹ በዚህ ሣምንት ከአልጄሪያ ይመለሳሉ በተባለው ቀን በትኬት ችግር አለመድረሳቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ የሸገር ደርቢ በሳምንቱ መጨረሻ ያወጣው መርሐ ግብር ላይ ለውጥ እንዲደረግ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይ ሆኖ ሸገር ደርቢ ለአንድ ሳምንት መራዘሙ ይታወሳል።
በአንፃሩ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሸገር ደርቢ ጥር 27 ቀን ብሎ ማሻሻያ ቢያደርግም በተባለበት ቀን ፈረሰኞቹ 87 ኛ አመት ታሪካዊ የምስረታ በዓላቸውን በታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት ክለቡን በገንዘብ ለማጠናከር ቀደም ብለው ያወጡት ፕሮግራም ላይ አሁን ለመለወጥ ግድ የሆነባቸው ይመስላል።
በመሆኑም ፈረሰኞቹ በታላቁ የገቢ ማስገኛ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ የቀን ለውጥ በማድረግ ክለቡ ዛሬ የቀን ለውጡን ይፋ አድርጓል
👇
“ስፖርት ማህበራችን ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ በፃፈው ህጋዊ ደብዳቤ መሰረት አክሲዮን ማህበሩ ጥያቄያችንን ተቀብሎ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታን ለአንድ ሳምንት ማራዘሙ ይታወቃል ፡፡ጥር 27 ቀን 2015ዓ.ም በ9፡00 ሰዓት አዳማ ላይ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር እንድንጫወት ፕሮግራም የተነደፈ በመሆኑ በዚህ እለት የሙዚቃ ኮንሰርቱን ለማከናውን የማይቻልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ፡፡በመሆኑም የሙዚቃ ኮንሰርቱ የካቲት 4 ቀን 2015 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የሚከናወን መሆኑን እንገልፃለን “
መረጃ
በቴሌግራም :-
በኢንስታግራም ገጻችንን :-
🔛ድረ ገጻችንን :-