ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” የህዝቡ ድጋፍ ለእኛ ትልቅ ስንቅ ነው : ለፋሲል ደጋፊዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እፈልጋለሁ” -አሰልጣኝ ስዩም ከበደ

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግን በ38ነጥብ በመረነት ላይ የሚገኘው የአሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚሰለጥነው ፋሲል ከነማ እስካሁን ያደረጋቸውን ጨዋታዎች ከአንድ ጨዋታ ሽንፈት በስተቀር ጉዞውን በድል እየተወጣ የዋንጫ ጉዞውን እያሳካ ይመስላል።ስኬታማው አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከሱፐር ስፖርት ጋር ቆይታ አድርጓል።የባህር ዳር ቆይታቸው ሙሉ ለሙሉየተሳካ ጊዜ ነበራችሁ ማለት ይቻላል ለሚለው ጥያቄ አሰልጣኙ ሲመልሱ “አዎ ። መጀመሪያም እንደተናገርኩት አንድ ጨዋታ ነው እኩል ለእኩል የወጣነው ከአምስት ጨዋታ አራቱን ሙሉ ጨዋታ አሸንፈናል። እና አሁን የሊግ አመራራችን ጥሩ በራስ መተማመን የሚሰጥ ነው። ከተከታዮቻችን ቀጣዩ የእረፍት ጊዜ ለእኛ በመንፈስም በአካልም የምንዘጋጅበት ጥሩ ጊዜ ይሆናል ብዬ አስባለሁ” በሚል ተናግሯልበሁለተኛው አጋማሽ የቡድኑን አጨዋወት ሂደት መለወጥ በተመለከተ አሰልጣኝ ሲመልስ”እሱ ላይ መታረም አለበት ። ፍላጎቴ እንደዛ አይደለም። ነገር ግን አንዳንዴ ተጫዋቾቼ 2 ለ 0 እንደሰፊ ውጤት በመውሰድ ራሳቸውን 100% ከመስጠት ትንሽ ቆጠብ አድርገዋል። …ያ ደግሞ ትንሽ ዋጋ ያስከፍላል። ወደ ፊት የሚታረም ቢሆንም አጠቃላይ ጨዋታውን ለመቆጣጠር ያደረግነው ነገር መልካም ነው። በሁለተኛው አጋማሽ ላይ የተቆራረጡ ስህተቶች ነበሩ። እንደዛም ቢሆን ዋነኛው ውጤቱ ነበርና ይህን ጨዋታ የማሸነፍ የግድ ፍላጎት ነበረን ተሳክቶልናል። እናም መልካም ነው ብዬ አስባለሁ” ሲል መልሹን ሰጥቷልየቡድኑ ጠንካራ ክፍል ወይም አሁን ላለው ውጤት ተጠቃሽ የትኛው ነው ለሚለው “አንደኛ የኳስ ቁጥጥሮች እየተሻሻሉ ሄደዋል። ሁለተኛ እንደ ቡድን የመከላከል ብቃታችን ጥሩ ነው። በተጨማሪ ደግሞ ተቃራኒ ሜዳ ገብተን የምናደርጋቸው ሙከራዎች በጣም ጥሩ ናቸው። እንደዛም ሆኖ የምንስታቸው አሉ። ለምሳሌ በመጀመሪያው አጋማሽ 3 ለ 0 ማረፍ እንችል ነበር። እንደነ በረከት ያገኙትን 100% ትኩረት ማድረግ አለባቸው …እነዚህ እነዚህ ነገሮች የሚሻሻሉ ግን በቡድኑ ላይ ግን ከፍተኛ ለውጦች ናቸው ብዬ አስባለሁ” ብለዋልየባህር ዳር የስንበት ቃሉ ምን እንደሆነ ለተጠየቀው” የባህር ዳር ቆይታችን በጣም ደስ ይላል። ባህር ዳር ላይ በርካታ የፋሲል ደጋፊዎች አሉ ።ከጎንደርም ከዚህም። ሁል ጊዜም ከጨዋታ በኋላ ከስታድየም ሆቴል አምስት ደቂቃ የሚፈጅ መንገድ አንድ ሰዓት ነው የሚፈጀው። የህዝቡ ድጋፍ ለእኛ ትልቅ ስንቅ ነው። እና ለመላው የፋሲል ደጋፊዎች እስከዚህ ያለንበት ደረጃ ድረስ እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እፈልጋለሁ” በማለት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከሱፐር ስፖርት ጋር በነበረባቸው ቆይታ ተናግሯል።