ሄኖክ አርፊጮ- ሀዲያ ሆሳዕና
ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“የሀዲያ ሆሳዕና ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ” – ሄኖክ አርፊጮ

ሄኖክ አርፊጮ- ሀዲያ ሆሳዕና

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ ረፋዱ የ24ኛ ሳምንት ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ 1 ለ 0 በሀዲያ ሆሳዕና ተሸንፎ የወጣበትን ጎል ለሀዲያ ሆሳዕና በ 17 ኛው ደቂቃ አምበሉ እና 17 ቁጥሩ ሄኖክ አርፊጮ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል። ከጨዋታው በኋላ ሄኖክ ከሱፐር ሰፓርት ጋር ቆይታ አድርጓል።

ስለጨዋታው
” ጨዋታው እንዳያችሁት ያው ከበድ ያለ ነበረ። እኛም ደግሞ ቡድናችን ከታች የመጡ ልጆች ነው ይዘን የገባነው። እንደቡድን ጥሩ ፉክክር ነበረ። እግዚአብሔር ረድቶን ጥሩ ውጤት ይዘን ወጥተናል።
የውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ እና ወሳኝ ጎል ከመሆኑ አንፃር የተሰማው
“ያው ምን ልበልህ ጎል በማስቆጠሬ እና ይህን ውጤት በማግኘቴ እጆግ በጣም ደስ ብሎኛል። የሀዲያ ሆሳዕና ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ”
ከሜዳ ውጭ ለቡድኑ አንዳን የገንዘብ ውጪ በመርዳት ፍቅሩን መግለፁ ይታወቃል ፣ ዛሬ ደግሞ ግል ማስቆጠሩ ለሀዲያ ሆሳዕና የተለየ ነገር ስለመኖሩ ?
“አዎ …ለእኔ እዚህ ደረጃ ላይ ለመድረስ ትልቁ ግንባር ቀደም ክለቤ ነው። የእዛውም አካባቢ ልጅ ነኝ። ያው የምችለውን ከፈጣሪ ጋር ጥሩ ነገር አድርጌያለሁ፤ ከዚህ በኃላም ጥሩ ነገር ይፈጠራል ብዬ አምናለሁ። ከክለቡ ጎን ነኝ በአጠቃላይ።
አምስት ታዳሚዎች ዛሬ ገብተዋል የነባር ተጨዋቾች መኖሮ ሜዳ ላይ ጠቅሟቸዋል?
” አዎ ይህን ስትለኝ በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው የጠየከኝ። እነዚህን ልጆች ባናገኛቸው በጣም አስቀያሚ ጊዜ ነበር የምናሳልፈው። የክለቡም ስራ አስኪያጅ ፣ ክለብ ማኔጅመንቱም ይሀን ነገር አድርገው አቅም እንዳለ የሚያሳይ ነገር ነውና ልጆቹም በጣም ከሚጠበቅባቸው በላይ እያደረጉ ያሉት ። ነገ ትልቅ ቦታ ትልቅ ደረጃ እናያቸዋለን ብዬ አምናለሁ ከፈጣሪ ጋር”
በጣም ረጅም ደቂቃ መከላከለቸው በተመለከተ
” ያው በጣም ጠንካራና ጥሩ ስብሰብ ካለው ቡድን ጋር ነው የተጫወትነው። እንደዛም ከመጫወታቸችን አንፃር ውጤቱ በጣም እንደምንፈልገው ከተከታታይ ሽንፈት ወደ አሸናፊነት በመምጣት በጣም ትልቅ ትግል ነው ያደረግነበት ነው። ጊዮርጊስ በጣም ጠነንካራና ጥሩ ቡድን ነው። ብዙ ብቃት ያላቸው ልጆች አሉ ።ግን ያንንም ተቋቅመን ሶስት ነጥብ ይዘን ወጥተናል”
ሀዲያ ሆሳዕና ሁለተኛ ሆኖ ለአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ያልፋል ?
” በፈገግታ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ አሁን ላይ እንዲህ ነው ብሎ መናገር የማይቻልበት ደረጃ ላይ ነው። ፣ ግን በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች የምንችለውን ነገር ከቡና ጋር ያለውን ጨዋታ ፍንጭ ይሰጣል ብዬ አምናለሁ ከፈጣሪ ጋር;እንደ ፈጣሪ ፍቃድ “