ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“ዛሬ ያስቆጠርኩትን ጎሎች በቅርቡ ለሚወለደው ልጄ እና ለትግራይ ህዝብ መታሰቢያ እንዲሆንልኝ እፈልጋለሁ”-ሪችሞንድ አዶንጎ

የድሬደዋው ከተማ ዛሬ አሸንፎ እንዲወጣ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ የዳኛው ፊሽካ ሲጠበቅ  የመጀመሪያውን ጎል ፣በተመሳሳይ የ90ኛው ደቂቃው ጨዋታ ተጠናቆ የዳኛው ፊሽካ ሲጠበቅ ጋናዊው አጥቂ  ሪችሞንድ አዶንጎ ሁለተኛውን ጎል አስቆጥሮ ድሬን ለድል አብቆይቷል። ሪችሞንድ አዶንጎ በድሬዳዋ ከተማ የዘንድሮው ቆይተው እነዚን ሁለት ጎሎች ብቻ ነው ያስቆጠረው። ከጨዋታው በኋላ ከሱፐር ስፖርት ጋር ቆይታ አድርጓል።

ጨዋታውን በተመለከተ
” ጨዋታው በጣም ከባድ ነበር። ከጅማሮው አውቅ ነበር። ይሁንና ከምንም በላይ በቅድሚያ ይህን ላደረገ እግዚአብሔርን ማመስገን እፈልጋለሁ። በተጨማሪም አሰልጣኞችን እና ተጨዋቾች በመሉ ለማሸነፍ የነበረን ታላቅ ተጋድሎ መጥቀስ እፈልጋለሁ ። ይህን ውጤት ብቻዬን ያመጣሁት አይደለም። በአንድ ላይ እንደ ቡድን ያመጣነው ውጤት ነው። ስለዚህ የዛሬው ውጤት እንዳለ ሆኖ ለቀጣዩ ጨዋታ ነው ትኩረታችን የሚሆነው”
በአመቱ ያስቆጠርካቻው ጎሎች የዛሬዎቹ ሁለት ወሳኝ ጎሎች ብቻ ከመሆናቸው አንፀር ደስታውን በተመለከተ ?
” (በፈገግታ) ዛሬ የደስታ ቀኔ ነው። ምክንያቱም የልጅ አባት በቅርቡ የምሆንበትም በመሆኑ ፣ ዛሬ ያስቆጠርኩትን ጎሎች በቅርቡ ለሚወለደው ልጄ መታሰቢያ እና ከዚህ በተጨማሪ ጎሉን ለትግራይ ህዝብ መታሰቢያ እንዲሆንልኝ እፈልጋለሁ። ስለዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ ማለት እችላለሁ “