አትሌቲክስ ዜናዎች

“ዛሬ በቶክዮ ኦሎምፒክ የታላላቆቼን ምሩፅ ይፍጠር፣ሀይሌ ገብረ ስላሴ እና ቀነኒሳ በቀለን ታሪክ በመድገሜ እንኳን ደስ ያለን እንኳን ደስ አላችሁ ” – አትሌት ሰለሞን ባረጋ

የወርቅ ሜዳሊያ ያሰገኘ ጀግናው አትሌት ሰለሞን ባረጋ

 

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በሰለሞን ባረጋ አማካኝነት ከ13 ዓመት በኃላ በኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡ ጀግናው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ ያሰገኘ የመጀመሪያው አትሌት ሆኗል። ጀግናው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች አፈትልኮ በመውጣት ርቀቱን በ27:ከ43.22 በሆነ ጊዜ በአስገራሚ መልኩ ማሸነፍ ችሏል።
በውድድሩ ከፍተኛ ፉክክር ያደረጉት ዮጋንዳውያኑ አትሌቶች የብር እና የነሀስ ሜዳሊያ አግኝተዋል። በቅርብ ዓመታት በርቀቱ ድንቅ ውጤቶች የሚያስመዘግበው ዮጋንዲዊው ጆሹዋ ቺፕቴጌና በሁለተኝነት ሌላው ዮጋንዳዊ ጃኮፕ ኪፕሊሞ በሶስተኝነት ሜዳልያ አግኝተዋል፡፡
ከድሉ በኃላ አትሌት ሰለሞን በረጋ ደስታውን ሲገልጽ

በውድድሩ የተሳተፉት ኢትዮጲያውያኑ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 4ኛ እና አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ 8ኛነት አጠናቀዋል፡፡ ከውድድሩ በኃላ አትሌት ሰለሞን በረጋ በማህበራዊ ገፁ በሚከተለው መልኩ ደስታውን ገልጿል ” ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬ በቶክዮ ኦሎምፒክ የታላላቆቼን ምሩፅ ይፍጠር፣ሀይሌ ገብረ ስላሴ እና ቀነኒሳ በቀለን ታሪክ በመድገም የ10ሺ ሜትር ሻምፕዮን በመሆኔ እንኳን ደስ ያለን እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ ፣ ይህንን ድል ለመላው ኢትዮጲያዊያን ማስታወሻ ይሁንልኝ” ብሏል