አፍሪካ

ዓይነ ስውሩ ታማኝ – የእግርኳስ ደጋፊ !

በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ኢትዮዽያ እግርኳስ ተወዳጅ ስፖርት ነው። ምንም እንኳ የእግርኳስ አፍቃሪው ቁጥር በየጊዜው መጨመር እና የሀገሪቱ የእግርኳስ ውጤት ፈፅሞ የተመጣጠነ ባይሆንም ኳስ በኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ተወዳጅ የስፖርት ዓይነት እና በርካታ ደጋፊዎች ያሉትም ስፖርት ነው።
ከዚህ ስፖርት ወዳድ ማህበረሰብ መካከል አንድ አስገራሚ እና ለብዙዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በተመሣሣይ ሁኔታ ውስጥ ላሉ አስተማሪ እና የፅናት ተምሳሌት የሆነውን ዓይነ ስውሩን ቀንደኛ የእግርኳስ ደጋፊ ላስተዋውቃችሁ።

ስሙ ተክሌ አበራ ይባላል ። የአራት ልጆች አባት ነው። ልጆቹን የሚያስተዳድረው እና ቤተሰቡን የሚመራውን በመንገድ ዳር ከሰል ሸጦ ነው ።
የመጨረሻ ልጁ ምንተስኖት መልኩን አያውቀውም ምክንያቱም የአይን ብርሃኑን ካጣ በኃላ የወለደው በመሆኑ እና አሁን ላይ ሁለቱም አይኖቹ ማየት አይችሉም።
የስፖርት ወዳድ የሆነ እና ስታዲየም በሚያዘወትሩ ተክሌ ይታወቃል። በተለይ በተለይ በኢትዮዽያ በርካታ ደጋፊ ክለቦች አንዱ ለሆነው የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ላለፉት 40 አመታት በታማኝ ደጋፊነቱ ለብዙዎቼ ተምሳሌት ነው። ተክሌ የሁለቱንም አይኖቹን ብርሃን ያጣው ከአስራ አምስት አመት በፊት በመኪና አደጋ በአዲስ አበባ ሰባተኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነበር። ታዲያ ይህ ቀንደኛ የኳስ አፍቃሪ የአይኖቹን ብርሃን ማጣቱ ከስታዲየም እና የኳስ ፍቅር ፈፅሞ አላራቀውም።

አስገራሚው ነገር ተክሌ በመኪና አደጋ የአይን ብርሃኑን ቢያጣም የሚወደዉን ክለብ መደፉን ግን ፈፅሞ አላቋረጠም። ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት ልጆቹ በስታዲየም የጨዋታውን እንቅስቃሴ በጆሮ እየነገሩት እሱም ድጋፉን ለሚወደው ክለብ ያሳያል።
አሁን ላይም የአይን ብርሃኑን ካጣ በኃላ የወለደው የመጨረሻ ልጁ ምንተስኖት ተክሌ ለአባቱ እያንዳንዷን ክስተት በጆሮው ይዘግብለታል።
ቀንደኛው አይነስውሩ የቡና ደጋፊ አባትም በዓይኑ አይቶት የማያውቀውን የልጁን የምንተስኖትን በእስትንፋስ በጆሮው እየሰማ በልቦናው የሚወደውን የኢትዮዽያ ቡና ክለብ እግኳስ ድጋፉን ይቀጥላል።


በርግጥ ተክሌ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ አብዛኛውን ጊዜ ልጁን ምንተስኖት እያስቸገረ በመሆኑ ምንተስኖት ከትምህርቱ እንዳይስተጓጎል አባት ይጨነቃል።
ሌላው ተክሌ የአይን ብርሃኑን በማጣቱ ምክንያት በተደጋጋሚ በተቆፈረ ጉድጓድ እየገባና በመንገድ ላይ ጉዳትም እየደረሰበት ነው። እንደውም ሁለት ጊዜ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበየቦት ሆስፒታል ለተወሰኑ ቀናትም ታክሟል።

የኢትየዽያ ቡና ቀንደኛ ደጋፊ ተክሌ በዓለም አቀፍ ደረጃ  የቀጥታ ሽፋን ባለው የDSTV ሰርጭት ዘንድሮውን የሸገር ደርቢ ነገ በቀጥታ ለመታደም ከልጁ ምንተስኖት ጋር በሐዋሳ ዮኒቨርስስቲ ተጉዟል። የኢትዮዽያ ቡና ቀንደኛ ደጋፊ ተክሌ የእርዳታ እጅም ይሻል ። በገንዘብ ለምትደግፉት ቁጥሩ ተክሌ አበራ..0920323245