ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ዐፄዎቹ ዋንጫውን በቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ ይረከባሉ – ዋንጫው ግን አሁንም አልደረሰም !

የ2013 የቤትኪንግ ሊግ አሸናፊ  የፋሲል ከነማ ቡድን

 

የ2013 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ለሆነው የፋሲል ከነማ ቡድን የዋንጫ ሽልማት ስነስርዓት በቀጣዮ ሳምንት ቅዳሜ ግንቦት 14/ 2013 ፋሲል ከነማ ከሐዋሳ ከተማ በሚያደርጉት ጨዋታ  የሻምፒዮናውን ዋንጫ እንደሚያንሳ  ታውቋል። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አዲስ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር የዋንጫው ስነስርዓት የፊታችን ቅዳሜ ለማካሄድ የተወሰነ ሲሆን የዋንጫ አሰጣጥ ስነስርዓት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መዘጋጀቱም ታውቋል። በአንፃሩ ዘንድሮ የተለየ የተሰኘው በስፓንሰር አድሪጊዎቹ የተዘጋጀው የሻምፒዮናው ዋንጫ አሁንም ከደቡብ አፍሪካ አለመግባቱ ታውቋል። ይሁንና ተጠባቂው ዋንጫ  ከስነስዓቱ ቀን በፊት የሚድርስም ይሆናል።
በተያያዘ ዜና የዘንድሮው የመጀመሪያው የቤትኪንግ ሻምፒዮና የዋንጫው ባለቤት ፋሲል ከነማ ቡድን የ1 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ እንደሚሆን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ቀደም ብሎ ማሳወቁ ይታወሳል።። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ቀደም ባሉት ወራቶች እንዳስታወቀው በ2013 የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሚሆነው ክለብ ከሚሸለመው ዋንጫ በተጨማሪ የ1 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ይሆናል። ሁለተኛ ሆኖ ለሚያጠናቅቀው  ክለብ የ700 ሺህ ብር ተሸላሚ ሲሆን 3ኛ ሆኖ ለሚጨርስ ክለብ ደግሞ የ500 ሺህ ብር ሽልማት ተሸላሚ ይሆናሉ ።
ዐፄዎቹ የዘንድሮው ውድድር አሸናፊ በመሆናቸው ዋንጫውን የፊታችን ቅዳሜ የሚረከቡ ሲሆን የዘንድሮው ውድድር ከተጠናቀቀ በኋላም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ለክለቦች   የገንዘብ እና የኮኮቦች ሽልማት እንደሚሰጥም ተገልጿል።