የዐዔዎቹ ጠንካራ ተከላካይ አንበሉ ያሬድ ባዬ ከጨዋታው በኋላ ከሱፐር ስፓርት ጋር ያደረገው ቆይታ አድርጓል።
ቡድኑ ሻምፓዮን በመሆኑ ደስታው እንዴት ይገለፃል ?
” ያው ዋንጫውን ስናነሳ ይበልጥ እንደሰታለን። ዋንጫውን ማንሳታችን እንዳረጋጥን በጣም ከፍተኛ ደስታ ውስጥ ገብተን ነበር። አሁን ደግሞ ጨዋታዎች አላለቁም እስከመጨረሻው ድረስ ጠንክረን እንጫወታለን። ይሄ የዋንጫ ቡድን ነው እስካሁንም እያሸንፍን ነው የመጣነው”
ኢትዮጵያ ቡና 0 ለ 0 የወጣበት ጨዋታ ነው ላይ ነበር ያረጋገጣችሁትና የትኛው ነበር የደስታ ስሜት የነበረው ?
” እኛ የማንንም ውጤት አንጠብቅም። የሌሎችን ውጤት እየጠበቅን አይደለም የተጫወትነው።እያንዳንዱ ጌም ለዋንጫ ነበር የተጫወትነው።እነሱም አሸንፈውን ቢሆን ይኸው እንደምታየው ነው። አረጋግጠንም እንደዚህ ነው የምንጫወተው። የእኛ ቡድን ጠንካራ ቡድን ነው። በዚህ ጨዋታ ነበር እናረጋግጣለን ብዬ ያሰብኩት።
የዲ ኤስ ቲቪ ዘመን ላይ ሻምፒዮና በመሆናቸው የተለየ ስሜት ?
” አዎ። ዋንጫም ተቀይሯል በቅርፅም ውበትም ተቀይሯል ( በፈገግታ) ፣ እናም በጣም ደስተኛ ነኝ የመጀመሪውን ዋንጫ በማሸነፋችን ፣ ታሪክም ነውና ። በዛ ላይ ሪከርድም እየሰበርን ነው። ያለመሸነፍ ሪከርድ እኛ ነን እና የአሁኑ ጠንከር ይላል ደስታውም እንደዛሬው”
ዘንድሮ ሻምፒዮና እኖሃናለን ብለህ ያሰብክበት ጨዋታ ነበረ ?
” ያው እኛ ተከታዮቻችንን እያሰነፍን በመጣንበት ጨዋታ ላይ ነው በቃ ሻምፒዮና በርግጠኝነት እንሆናለን ብዬ ያሰብኩት። ከጊዮርጊስ ጀምረን ቡና እያልን ስናሸንፍ የዛን ጨዋታ ጊዜ ነው ያሰብኩት”
የባህርዳር ቆይታቹ ጊዜ ማለቀ ነው ሻምፒዮና እንደምትሆኑ ውስጥህ የነገረኸ ?
” ከጅማ ጀምሮ፣ በይበልጥ አራቱን ተከታይ ስናሸንፍ። ከጅማም ባህርዳርም እና ይበልጥ ያረጋገጥኩት ባህርዳር ነው”
ስለቀጣዩ ጨዋታዎች
“እኛ የተለየ ቡድን ይዘን እንቀርባለን ብዪ አላስብም። በየጨዋታው የተጨዋቾች ቅያሪ ሊኖር ይችላል። ግን ጨዋታችን ወሳኝ ወሳኝ ነው። ጠንካራ ቡድን ይዘን ነወቀ ዠምንቀርበው”
ያሬድ አዲሱን ዋንጫ ለማንሳት እራሱን አዘጋጅቷል
” አዎ። (በፈገግታ )ክብደቱን አስመልክቼ በለየም አየሰራሁ ነው ለማንሳት ‘ ( በፈገግታ) “