የ25ኛው ሳምንት የእሁድ ረፋድ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ተጋጣሚውን ጅማ አባጅፋርን 4 ለ 1 ያሸነፉበት ናይጀያዊው አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ ሃትሪክ ሰርቶ ቡድኑን ከተቀላቀለ በኋላ ያስቆጥርውን የጎሎችን ቁጥር ሰባት ያደረሰበት ነበር። ከጨዋታው በኋላ ከሱፐርስፓርት ጋር ቆይታ አድርርጓል።
ለቡድኑ ወሳኝ ጎል እና ሃትሪክ ማስቆጠሩን በተመለከተ የተሰማውን ስሜት
” በጣም ደስተኛ ነኝ ። የዛሬውን ሃትሪክ ያስቆጠርኩን ጎሎች የባለቤቴም ልደቷ መሆኑ ድርብ ደስታ ነውና በጣም ደስተኛ ነኝ። አመሠግናለሁ”
ቡድንን የተቀላቀለው ከሁለተኛው ዙር በኃላ ቢሆንም ሰባት ጎሎች ማስቆጠሩ
” ጥሩ ጊዜ ነው ማለት እችላለሁ ፣ መጥፎ አይባልም። ዋናው ዓላማዬ ቡድኔ በፕሪምየር ሊጉ እንዲቆይ ነው ስለዚህ ይሄ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው። በጣም ደስተኛ ነኝ “
ጎል ሲያስቆጥር ደስታውን የሚገልፅባነው የተለያዩ መንገዶች ሲሆን እንዱ የእጅ ሰዓት በተማመልከት….
” አዎ ….ደስታ አገላለፄ ለደጋፊዎቼ ከማሳየት ጋር የተያያዘ ነው……”
በዛሬው ውጤት የተሰማው ደስታ
” በጣም ደስቸኛ ነኝ። ከትላንት ጀምሮ ለማሸነፍ በሚል ነበር ስንነጋገር የነበረው ቃልም ገብተን ነበረ ስለዚህ አድርገንዋል። ደስተኛ ነኝ በውጤቱ በጣም
በሊጉ ረጅም አመት ከመጫወቱ አንፃር የዘንድሮው ውድድር DSTV ከመታየቱ አንፃር ለየት ስለማለቱ
” በጣም ጥሩ ነገር አይቻለሁ፣ በDstv ብቻ ሳይሆን ብዙ ለውጦች አሉ”