Uncategorized

-ዋልያዎቹ ያውንዴ ደርሰው ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል !

ለካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ ወደ ስፍራው የተጓዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ልዑካን አባላት ዛሬ ከሰዓት ካሜሩን – ያውንዴ ደርሷል። በትላንት ምሽቱ የሽኝት ፕሮግራም በስካይ ላይት ሆቴል በተሳካ መልኩ ያስተባበረው ሲሳይ አድርሴ ፕሮሞሽን በያውንዴም ከሳምንት በፊት በመጓዝ እና የኮሚዩኒቲው አባላትን በማስተባበር ዋሊያዎቹን በደማቅ ሁኔታ ዛሬ ተቀብለው የእንኳን ደህና መጣችሁ የኬክ ቆረሳ ተደርጎላቸዋል።