የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማዳጋስካር አቻው ጋር ነገ ከቀኑ 10 :00 ሰዓት በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጨዋታውን ያደርጋል።
ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ለማለፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎች ይቀሩታል። በመጋቢት 15 (ነገ ) በባህር ዳር ስታዲየም ከማዳጋስካር ጋር አድርጎ ከአንድ ሳምንት በኃላ መጋቢት 21 ደግሞ ከኮትዲቯር ጋር በአቢጃን እንደሚጫወቱ ይታወቃል።
የኢትዮዽያ በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ ” K” ከአይቮሪኮስት ፣ ከማዳጋስካር እና ከኒጀር ምድብ ውስጥ በስድስት ነጥቦች በሦስተኛ ደረጃ ይገኛል።
ብሔራዊ ቡድኑ በምድብ ማጣሪያው ያደረጋቸውን አራት ጨዋታዎች ሁለቱን አሸንፎ በሁለቱ ተሸንፏል ። ወደ ኒጀር ተጉዞ በኒጀር በሜዳው 1 ለ 0 ከተፈሸ በኃላ በባህዳር ስታዲየም የመልስ ጨዋታው ኒጀርን 3 ለ 0 አሸንፏል። የአይቮሪኮስትን ብሔራዊ ቡድንን በባህር ዳር ሰታዲየም በ2 ለ1 ውጤት አሸንፏል።
በአንፃሩ በማዳጋስካር ያደረገውን ጨዋታ በማዳጋስካር 1 ለ 0 ተሸንፏል። ይህን ጨዋታ አስታውሶ በቅርቡ የማዳጋስካሩ አምበል አቤል አኒኬት ለቢቢሲ ስፖርት እንደተናገረው “እውነት ነው 1 ለ 0 አሸንፈናል : ግን ደግሞ አብዛኛውን ጨዋታ የበላይነት እነሱ ነበራቸው ፡፡ በተለይም ጥሩ ተጫዋቾች አሏቸው” በማለትም ተናግሯል።
እ.ኤ.አ 2013 የአፍሪካ ዋንጫ በኃላ ዋልያዎቹ አሁን በአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ትልቅ ዕድል አላቸው። ሆኖም ከማዳጋስካር እና ከአይቮሪኮስት የሚያደርጉት ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ትልቅ ፍልሚያ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ለኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን በተለይም ከማዳጋስካር ጋር ዕረቡ የሚያደርጉት ጨዋታ ከሁለት በላይ ጎሎች አስቆጥረው ማሸነፍ ይኖርባቸዋል።ምክንያቱ ደግሞ በመጀመሪያው ጨዋታ ማዳጋስካር ኢትዮዽያን 1ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፏ ነው። በመሆኑም ይህንን ጨዋታ ማሸንፍ ምንአልባትም በቀጣይ ጨዋታ በአቻ ውጤት ቢለያዩ እና ከማዳጋስካር ጋር እኩል ነጥብ ቢሆኑ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ቡድኖቹ በእርስ በርስ ግንኙነት ወቅት አብላጫ ጎል ያስቆጠረው ይለፍ የሚለው ህግ ተግባራዊነት የማለፍ ዕድል ይኖራል ።
በዚህም በረቡዕ ጨዋታ ከፍተኛ ጎል ያስቆጠረው ቡድን ሀላፊ በሚለው ህግ የማለፍ ዕድልም በሁለቱም ቡድኖች ስለሚታሰብ ጨዋታው ለዋልያዎቹም ለማዳጋስካርም ከፍተኛ ፍልሚያ ነው ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኩል ይህን ጨዋታ በግድ ማሸነፍ እና ኮትዲቯርንም እንዲሁ ማሸነፍ ይኖርባቸዋል። ለዚህ ደግሞ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ወሳኙን አጋጣሚ እውን ለማድረግ የሚችሉበት ሰአት አጋጣሚ ቀድመው ያሰሉት ይመስላል። አሰልጣኙ የብሔራዊ ቡድኑን ተጨዋቾች ምርጫ ከማካሄዳቸው በፊት በኮሮና ምክንያት የተፈጠረው አጋጣሚ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በተወሰኑ ስታዲየሞች በመሆኑ አብዛኞቹን ጨዋታዎች በስታዲየሞች ተገኝተው ሲከታተሉ እና ከዚህ ቀደም የሚሰራበትን የተጨዋቾች ምርጫን አሰራር ሰብረው ታይተዋል ። ከዚህ ቀደም አሰልጣኞች ሁሉንም የሊጉ ጨዋታዎች ተዟዙረው በተለያዩ ከተሞች ሄደው ማየት ስለማይችሉ የተጨዋቾች ምርጫው ላይ ተፅዕኖ ነበረው።
አሰልጣኙ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በአካል ተግኝተቸው የመረጧቸውን 27 ተጨዋቾች ከሀገሩቱ ሊግ ውስጥ መርጠው በሁለት ምዕራፍ ዝግጅት አድርገዋል። በአንፃሩ በብሔራዊ ቡድኑ ከአገር ውጪ በሚገኝ ሊግ የሚጫወት ተጫዋች በቡድኑ ያለው ሽመልስ በቀለ ብቻ ነው። በአንፃሩ እ.ኤ.አ 2013 የአፍሪካ ዋንጫ ላይ የተሳተፉት የቡድኑ አምበል ጌታነህ ከበደ ፣ ሽመልስ በቀለ እና ጀማል ጣሰው በዚህ ቡድን መሪ ናቸው።ከዚህ በተጨማሪም በሀገሪቱ የቤትኪን ፕሪሚየር ሊግ ላለፉት ወራቶች ጎልተው የታዩት በሊጉ የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች ደርጃን በ21 ጎሎች የሚመራው አቡበከር ናሲር ፣ በ15 ጎሎች በሁለተኛነት የሚከተለው ሙጂብ ቃሲም እንዲሁም ሱራፌል ዳኛቸ፣ አማኑኤል ገ / ሚካኤል ሌሎች ጥሩ ብቃት ላይ የሚገኙ ተጨዋቾችን አካተው ኢትዮጵያን ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ ቆረጥው ተንሰተዋል። በተጨዋቾቹም በኩል ይሄው ከፍተኛ ሞራል ጎልቶ ይታያል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች አንድም ጊዜም ሽንፈትን ያላስተናገደው የባህርዳር ስታዲየም የነገውን ጨዋታ ያለ ተመልካች ያስተናግዳል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታውን ለካፍ ቀድሞ ጥቂት ተመልካቾች እንዲገኙ ባለማስፈቀዱ በነገው ጨዋታ የሚኖረው በክቡር ትሪቩን በኩል ጨዋታውን ለማየት ከፌዴሬሽኑ በኩል ፍቃድ ያገኙ የሜዲያ ባለሙያዎች እና ጥቂት የተመረጡ ተመልካቾች ሊኖሩ እንደሚሉ ይጠበቃል። የነገውን ጨዋታ በቀጥታ ስርጭት የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እና CANAL + SPORT 3 የሚያስተላልፉት ይሆናል።
መልካም እድል ዋልያዎቹ