በካሜሩን አስተናጋጅነት ለ33ኛ ጊዜ በሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት የሚደረግበት ይፋ ሆኗል። የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓቱን ቀደም ብሎ ቀኑን June 25 በሚል ካሳወቀ በኃላ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ይታወሳል። ይሁንና ካፍ የመጨረሻ ዕጣ ማውጣት ድልድል ቀኑን እሁድ ነሐሴ 9/2013 (August 15, 2021) ቀን በያውንዴ በሚገኘው ፓሌስ ዴ ኮንግረስ እንደሚካሄድ አሳውቋል።
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከ2021 ወደ 2022 ዓ.ም የተዘዋወረው የካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ የምድብ ድልድል የዕጣ ማውጣት ቀን ሲታወቅ ከስምንት ዓመት በኃላ የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ሀገራት ይታወቃሉ ማለት ነው።
የ2022 የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊዎች 24 የአፍሪካ አገራት የሚሳተፉ ይሆናል ። ካሜሩን(አዘጋጅ)፣ኢትዮዽያ፣ሴኔጋል፣አልጄሪያ፣ናይጄሪያ፣ሞሮኮ፣ቱኒዚያ፣አይቮሪኮስት፣ማሊ፣ጊኒ፣ቡርኪናፋሶ፣ግብፅ፣ጋና፣ጋቦን፣ሞሪታኒያ፣ኬፕ፣ቨርዴ፣ዛምቢያ፣ጊኒ ቢሳው፣ሴራሊዮን፣ኮሞሮስ፣ጋምቢያ፣ማላዊ፣ሱዳን ፣ኢኳቶሪያል ጊኒ ይሆናሉ።