ዜናዎች

ዋልያዎቹ ወደ አይቮሪኮስት ለመጓዝ ከባህርዳር ተነስተው ጉዞ ጀምረዋል !

ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ትላንት በማጣሪያ ጨዋታው ማዳጋስካርን  በ 4 ለ 0 ድል ያሸነፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ እና የመጨረሻ ወደ ሆነው ጨዋታ ጉዞውን ጀምሯል።የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ከትላንቱ የማዳጋስካር ድል በኃላ አሁን ከባህርዳር ተነስተው ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ጀምረዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አዲስ አበባ ዛሬን አዳሩን አድርጎ  ወደ አይቮሪኮስት ጉዞውን  ነገ  የሚያደርገው ይሆናል።
በቡድኑ ውስጥ ሁሉም ተጨዋቾች በአሁኑ ሰአት በሙሉ ጤንነት ላይ የሚገኙ መሆኑን ታውቋል።  ። መጠናኛ ጉዳት አስተናግዶ የነበረውን እና የዋልያዎቹ ጠንካራ ተከላካይ ያሬድ ባዬ በመልካም ጤንነት ላይ መሆኑን ከኢትዮ ኪክ በነበረን አጭር ቆይታ አረጋግጠናል።ዋልያዎቹ በማዳጋስካር ብሔራዊ ቡድን ላይ የጨዋታ እና የውጤት የበላይነትን በማሳየት ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ መቅረባቸውን አሳይተዋል። ይሁንና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ መጋቢት 21 አይቮሪኮስትን አቢጃን ላይ የሚያደርገው ጨዋታ ሁሉንም ነገርየሚያረጋጥ ይሆናል።