ዜናዎች

ዋልያዎቹ ከሴራሊዮን ጋር በህዳር ወር የሚያደርጉት ጨዋታ በየትኛው ሜዳ ይካሄዳል ?

◼🔘 የአዲስ አበባ ስታዲየም የትሪቩን ወንበሮች አሁንም አልተገጠሙም !
👇
የአዲስ አበባ ስታዲየም በ2016 መጀመሪያ ወራት ጀምሮ የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታዎች እና የብሔራዊ ቡድኑን ጨዋታዎች ማስተናገድ እንደሚጀምር የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ ከወራቶች በፊት መናገራቸው ይታወሳል። በአንፃሩ የአዲስ አበባ ስታዲየም የዕድሳት ሂደት አሁንም ጥገና ላይ ነው። እንደሚታወቀው የዕድሳቱ ሂደት ከተጀመረ በኃላ በስታዲየሙ 22 ሺ ወንበሮችን የመግጠም ሂደት ፣ የመጫወቻ ሜዳው ሳር የማልበሱ ሂደት እና በውስጥ የሚገኙ የመፃደጃ ክፎሎችና ሌሎችም ነገሮች ዕድሳት በኋላ በተባለው ፍጥነት ከመጨረስ ይልቅ ስራው ብዙም ለውጥ ካለመኖሩ አንፃር አሁን ላይ ዕድሳቱ ተቋርጦ ነውም ያስብላል ። የስታድየሙ ወንበሮች በአብዛኛው የተገጠሙ ቢሆንም በትሪቩን በኩል ወንበር አልተገጠመም፣ ይልቁንም ከስታዲየሙ በዋናው በር መግቢያ በኩል ጥገና ላይ መሆን ለማሳየት ስታድየሙ በእንጨት ድጋፍ ታጥሮ ይገኛል።
እንደሚታወቀው የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን November 13 /2023 ( ህዳር 3 ) ከሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን ጋር ፤ በሳምንቱ ደግሞ ከቡርኪናፋሶ ጋር የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የሜዳ ጨዋታዎች ያደርጋል። ብሔራዊ ቡድኑ ከወር በኋላ ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የት ሜዳ ላይ እንደሚጫወት አሁን ላይ የታወቀ ነገር የለም።
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በኩል ጨዋታው አበበ ቢቂላ ስታዲየም እንዲሆን ፍላጎት ቢኖርም አሁንም የዋልያዎቹ በሜዳ ችግር ጨዋታቸውን ከኢትዮጵያ ውጭ እንደሚያካሂዱ መረጃዎች ያመለክታል።
እንደተጠቀሰው የአዲስ አበባ ስታዲየም ከዕዳሳት ጋር በተያያዘ ለህዳር ወር ጨዋታ የሚደርስ ባለመሁኔታ የባህርዳር ስታዲየም እድሳት እና አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ፣ የድሬዳዋም ዕድሳት በመሆኑ ጨዋታው ከኢትዮጵያ ውጪ ይሆናል የሚለው መረጃ ቢያመለክትም ፌዴሬሽኑ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንዲካሄድ ለማድረግ ለፊፋ ጥያቄ አስገብተዋል ።
ይሁንና ፊፋ የፌዴሬሽኑን ጥያቄ ይቀበላል የሚለው ምላሹ ያልታወቀ ሲሆን ፊፋ የፌዴሬሽኑን ጥያቄ ተቀባይነት ከሌለው ዋልያዎቹ እንደተለመደው ጨዋታቸውን በሌላ ሀገር ሜዳ ላይ የሚያደርጉ ይሆናል።