ዜናዎች

ዋልያዎቹ ከማዳጋስካር የሚያደርጉት ጨዋታ በቀጥታ ስርጭት ሽፋን ይኖረዋል

🔴 CANAL + SPORT 3 ይተላለፋል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ዕረቡ ከማዳጋስካር አቻቸው ጋር የሚያደርገውን ወሳኝ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በቴሌቪዥን እና በሬዲዮ በቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፈው መሆኑ ታውቋል። በተመሳሳይ ጨዋታውን CANAL + SPORT 3 የተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያስተላልፈው ሲሆን የDSTV ተንቀሳቃሽ መኪናም ለዚህ ተግባር በባህርዳር ስታዲየም ይገኛል።እንደሚታወቀው ይህንን ጨዋታ የማስተላለፍ መብቱ ያለው የአፍሪካ የእግር ኳስ የበላይ አካል የሆነው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ብቻ መሆኑ ይታወቃል። ይሁንና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በኬኒያ ከሚገኘው የዲኤስቲቪ የበላይ ከሆነው ካምፖኒ ጋር ባደረጉት ስምምነት ጨዋታው CANAL + SPORT 3 በተባለ ጣቢያ የቀጥታ ሽፋን የሚያገኝ ይሆናል። የሱፐር ስፖርት በቀጣይ ዕሮብ የሚኖረው የስራ ድርሻ ጨዋታውን በቀጥታ ስርጭት ለማስተላለፍ የካሜራ እና ተንቀሳቃሽ ስቲዲዮ ማከራየት ይሆናል። በኬኒያ የሚገኘው የዲኤስቲቪ የበላይ ከምፖኒ እና በካፍ ስምምነት መሠረት ጨዋታው በቀጥታ ስርጭት CANAL + SPORT 3 የሚያስተላልፉት ይሆናል። የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በተንቀሳቃሽ ስቱዲዮ (መኪና) በቀጥታ ስርጭት በአዲስ አበባ፣ በጅማ ፣ በባህርዳር የነበረው ሱፐርስፖርት በቀጣይ ዕሮብ ከሚኖረው የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኃላ ተንቀሳቃሽ ስቲዲዮ ወደ ቀጣይ የቤትኪንግ አዘጋጅ ከተማ ድሬደዋ ያመራል።