የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአምስት ሰዓታት በረራ በኋላ አክራ አየር ማረፊያ የደረሱ ቢሆንም ለኢንተርናሽናል በሪራ ከኢትዮጵያ የሰጡት የኮቪድ ምርመራ ውጤት አክራ ላይ ባለመቀበላቸው ቡድኑ ዳግም ምርመራ አድርጎል። በዚህም ለእያንዳንዱ ተጨዋች ከ6800 የኢትዮጵያ ብር በላይ ተከፍሎ የኮቪድ ምርመራ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
በተያያዘ መረጃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጋና አቻው ጋር ዓርብ ምሽት በ 4:00 የሚደርጉት የ2022 የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ በፊፋ ዩቲዩብ ቻናል በቀጥታ የሚታለፍ መሆኑ ታውቋል። ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ፊፋ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከሚያስተላልፋቸው መሃል የኢትዮጵያ እና የጋናም ጨዋታ በፊፋ የዩቲዩብ ቻናል የፊታችን ዓርብ ምሽት የሚያተላልፍ ይሆናል ።
የቀጥታ ሽፋን በዩቲዩብ ቻናሉ ለማየት ሊንኩ
https://www.youtube.com/watch?v=VdrZiWE1oK8
Gana vs ethiopia
Etiopya