ዜናዎች

ዋልያዎቹ በፊፋ የደረጃ ሰንጠረዥ ከዓመታት ቆይታ በኋላ ከፍተኛ መሻሻል አሳዩ!

ዛሬ ይፋ በሆነው የፊፋ ወርሃዊ የአገራት ደረጃዎች መሰረት ኢትዮጵያ የወንዶች ብሔራዊ ቡድኑ ከዓመታት ቆይታ በኋላ በደረጃ ሰንጠረዥ ከፍ  ማለቱን  ቀጥሏል።  
በኮሮና ምክንያት የአገራት ውድድር መቋረጡን ተከትሎ በ2019/2020 መቋረጥ አጋጥሞት የነበረው ወርሃዊ የደረጃ ሰንጠረዥ ባለፈው ዓመት ውድድሮች መቀጠላቸውን ተከትሎ ፊፋ የዓለም አገራት ወርሀዊ የደረጃ ሰንጠረዥን ይፋ ማድረጉን ቀጥሏል።
በዚህም መሰረት  በወርዊው የደረጃ ሰንጠረዥ ዋልያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ኮትዲዮቫርን 2ለ1 በማሸነፉን የአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን ተከትሎ የሦስት ደረጃዎች ማሻሻል  በዚህ  ወር አሳይተዋል።
እንደሚታወሰው ዋልያዎቹ በፈረንጆቹ November, 2019 ከ151ኛ ደረጃ ወደ 146ኛ ካሻሻሉ በኃላ የ146ኛ ደረጃን ማሻሻል ሳያሳዩ እስከ April 2021 ላለፉት ዓመታት ይዘውት መቆየታቸው ይታወሳል።
በApril 2021 ዋልያዎቹ 140ኛ ጀረጃ  በመያዝ በወሩም May እንዲሁ 140ኛ ደረጃ ከያዙ በኃላ አሁን ደግም የ137ኛ ደረጃ በመያዝ መሻሻል አሳይተዋል። ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ለደረጃው መሻሻል ምክንያት ሆኗል።