ዜናዎች

ዋሊያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን ተከትሎ የ6 ሚሊየን ብር የማበረታቻ ሽልማት ሊበረከትላቸው ነው !

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን   ዛሬ ረፋድ ባካሄደው  ስብሰባ   የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል።
1. ከ8ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመለሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት የ6ሚሊዮን ብር ሽልማት እንዲሰጣቸው እና ሽልማቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያዉን በሚያደርግበት ሐዋሳ ከተማ እንዲሆን ውሳኔ ተላልፏል።
2. ለክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ከ17ዓመት በታች ውድድር ላይ ለሚሰሩት ስራ ድጋፍ የሚሆን የ3ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ማለትም የ300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር ) ድጋፍ ለእያንዳንዱ የክልል እና የከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች እንዲሰጥ እና ስራው በአግባቡ ስለመሰራቱ እያንዳንዱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክትትል እንዲያደርግ ተወስኗል።
ምንጭ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን