የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ብድን አማካይ ተጫዋች ጋቶች ፓኖም ከግብፁ ክለብ ከሀራስ አልሁዳድ እና ሳውዲው የሁለተኛ ዲቪዚዮን አል አንዋር ክለብ ጋር የነበረው የኮንትራት ጊዜ ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁ ወደ አገሩ መመለሱ ይታወሳል። በአገሩ ከአራት ቆይታ በኃላ በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው የሚሰለጥነውን ወላይታ ድቻዎችን በመቀላቀለ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታውን ለአዲሱ ክለቡ ዛሬ ተሰልፎ የመጀመሪያውን ጎልም አስቆጥሯል።ከዛሬው ጨዋታ በኃላ ጋቶች ከሱፐር ስፖርት ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።ወደ ኢትዮጵያ ከተመለስክ በኃላ በመጀመሪያ ጨዋታው የመጀመሪያ ጎል ማስቆጠሩን ተጠይቆ ጋቶች ሲመልስ ” ያው ወደ አገር ቤት ከተመልስኩ ከአራት ወራት በኃላ ነው ልምምድ የጀመርኩት። ጎል በማስቆጥሬ ሶስት ነጥብ በማግኘታችን በጣም ደስ ብሎኛል” ብሏልበግበፅ እና በሳዊዲ ሊግ ከመጫወቱ አንፃር ጨዋታዎቹ በDstv መተላለፉ ለተጫዋቾች የሚሰጠው ጠቀሜታን ተጠይቆ ጋቶች ሲመልስ ” መተላለፉ ቢያንስ ለሁሉም ተጨዋቾች ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም በፊት በውጪ ክለቦች ለመጫወት ቪዲዮ አይገኝምና አሁን ደግሞ Dstv በመምጣቱ ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረገ ተጨዋች ጥሩ ቪዲዮ እንደሚያገኝ እና ወደ ውጭ ለመውጣት ቅርብ ነው ማለት ነው። ” በማለት ተናግሯልከወላይታ ዲቻ ጋር በዘንድው ውድድር ስሚያስበው ተጠይቆ የአማካይ ተጨዋቹ ጋቶች ሲመልስ ከቡድኑ ጋር ጥሩ ውጤትን ይዞ ማጠናቀቅ እንደሚፈልግ ተናግሯል። በመጨረሻም ዛሬ ያስቆጠረውን ጎል ለማን ማስታወሻ ይሁን ለሚለው ጋቶች በፈገግታ “…ጎሉን ለጩጨዋ ወይም ለህፃን ሴት ልጁ ይሆን ብሏል” ጋቶች ፓኖም